walia tenders

walia tenders

አርጂ ገበያ


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁማር ቦሌ / ክ / ከ / አ / ግ / ከ / ቅ / ጽ / ቤት 002/2012 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል 

  • ሎት አንድ:- የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 
  • ሎት ሁለት : የፅዳት ዕቃዎች 
  • ሎት ሦስት:- ልዩ ልዩ ቋሚ አላቂ እቃዎች 
  • ሎት አራት- የደንብ ልብስ 
  • ሎት አምስት፡- የህትመት ስራዎች 
  • ሎት ስድስት: ቋሚ ዕቃዎች 
  • ሎት ሰባት፡- የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች እና የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ማሽን መለዋወጫ ግዥ ለዓመት የሚቆይ 
  • ሎት ስምንት፡-የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ለ1 ዓመት የሚቆይ 
  • ሎት ዘጠኝ፡-የተለያዩ የመኪና ዲኮሬሽን ዕቃዎችና ንጣፍ፡ ስራ 
  • ሎት አስር፡- የፓርቲሽን ስራ 
  • ሎት አስራ አንድ፡-የባሊኮኒ/ካውንተር /counter/ ጠረጴዛ ስራ 

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል 

  1. ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይንም አገልግሎት ግዥ ጋር የተዘጋጀ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃዎችን (ክሊራንስ) ከግብር አስገቢው መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ:: 
  2. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተካተቱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ :: 
  3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን እና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ማቅረብ የሚችሉ 
  4. የአገር ውስጥ የድጋፍ ኣቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት (በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት) ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ 2089.00 ብር/ ሁለት ሺህ ሰማንያ ዘጠኝ ብር/ ለሎት ሁለት ሶስት እና፤አራት 500.00 ብር / አምስት መቶ ብር/ ለሎት አምስት 1000.00 ብር / አንድ ሺህ ብር/ ለሎት ስድስት 3000.00 ብር ሶስት ሺህ ብር/ ለሎት ሰባት፤ ስምንት፤ዘጠኝ፣አስር እና አስራ አንድ 2% ለእያንዳንዳቸው ብር ሎቶች በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው: CPO መሰራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል አድራሻ መሆን አለበት። 
  5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6:30 ሰዓት ጨምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መከፈቻው ቀን ድረስ አንበሳ ጋራዥ በስተጀርባ ከሚገኘው የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ከግዥ ቡድን እራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 404 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ:: የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያጠቃለሉ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባችሁ። 
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጥንቃቄ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11 ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይገባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በግዥ ቡድን ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል። 
  7. ሰነዱን በሚመልሱበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃ መያያዝ አለበት 
  8. አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ
  9. የጨረታው አሸናፊ የአሽናፊነት ደብዳቤ እንደደረሰው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር ፐርሰንት) CPO በማስያዝ፤ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል:: 
  10. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ናሙናዎችንም ለንብረት አስተዳደር ክፍል ማስረከብ አለባቸው። 
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ስልክ ቁጥር 0116-39-42-35 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 

ገቢዎች ቢሮ 

የቦሌ ክ/ ከተማ አነስተኛ ግብር 

ከፋዮች ቅ/ ጽ/ ቤት 

አዲስ አበባ

 

 




___________________________________________________________________________________

Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Electrical and Electronics, Electronics Equipment, Food and Beverage, Catering Service, Furnishing and Fixture, Carpets and Curtains, Partition Related, Furnitures, Other Furniture, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Public Relations and Advertising, Event Organizing, Purchase., Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing

Posted Date : አዲስ ዘመን ሐሙስ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ . ም   

Deadline : 2020-03-22 [መጋቢት 13]


________________________________________________________________

ጽ/ቤቱ የመስተንግዶ አገልግሎት ፣የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የኮምፒዩተር ጥገና አገልግሎት፣ የጉልበት ሰራተኛ አገልግሎት፣ ዲኮር ፣ የደንብ ልብስ፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቢሮ ቀለም ቅብ ፣ የዘር አገልግሎት፣ የቧንቧ መስመር መቀየር፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡|በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት|

Deadline : 2020-03-24 [መጋቢት 15]

ጽ/ቤቱ የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣የፅዳት ዕቃዎች፣ልዩ ልዩ ቋሚ አላቂ እቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ፣የህትመት ስራዎች ፣ቋሚ ዕቃዎች ፣የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች እና የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ማሽን መለዋወጫ ግዥ ለዓመት የሚቆይ ፣የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ለ1 ዓመት የሚቆይ ፣የተለያዩ የመኪና ዲኮሬሽን ዕቃዎችና ንጣፍ ስራ ፣ የፓርቲሽን ስራ ፣የባሊኮኒ/ካውንተር /conter/ ጠረጴዛ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል |በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ|

 Deadline : 2020-03-22 [መጋቢት 13]

ጤና ጣቢያው የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ የጥገና እቃዎችና ጥገና፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ህትመት፣ እንዲሁም ቋሚ እቃ ግዢ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል |በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 12 ጤና ጣቢያ| 

 Deadline : 2020-03-22 [መጋቢት 12]

ባንኩ የባንክ ቅጾች ህትመት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ |የኢትዮጵያ ልማት ባንክ | 

Deadline : 2020-03-31[መጋቢት 22]

ኤጀንሲው ከታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል |የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ |

Deadline : 2020-03-22 [መጋቢት 12]

ጽ/ቤቱ የፅህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣የፅዳት ዕቃዎች፣የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ደንብ ልብስ፣ህትመት፣የመስኮት መጋረጃ /የሻተር/ ስራ፣የታሸገ ውሃ፣ኮምፒውተር፣የቢሮ ፖርቲሽን ስራ፣የጀነሬተር ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል |በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት | 

Deadline : 2020-03-25[መጋቢት 16]

መ/ቤቱ የሠራተኞች ደንብ ልብስ ፣የጽህፈት መሣሪያዎች እና የጽዳት መሣሪያዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል |የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር| 

Deadline : 2020-04-03 [መጋቢት 25]


Back to Home





Report Page