walia tenders

walia tenders

አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)


የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት (Addis Ababa City Government Revenue Authority-Arada Sub City Small Tax Payers Branch Office) -002/2012

ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ለ2012 በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ፡

  • ሎት 1፡- የፅህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 2 : የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3፡- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
  • ሎት 4፡- ደንብ ልብስ
  • ሎት 5፡- ህትመት
  • ሎት 6፡- የመስኮት መጋረጃ /የሻተር/ ስራ
  • ሎት 7፡- የታሸገ ውሃ
  • ሎት 8፡- ኮምፒውተር
  • ሎት 9፡- የቢሮ ፖርቲሽን ስራ
  • ሎት 10፡- የጀነሬተር ጥገና

በ2012 የበጀት ዓመት ለ2ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ብቁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN) ያላቸው መሆኑን፣
  3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
  4.  የዕቃዎቹን ዝርዝር ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ለተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች የማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ ብር / በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፣
  5. ተጫራቾች ቴክኒካል ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች “አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ” በተጨማሪምለእያንዳንዱ ሎት የፋይናንሻል የዋጋማቅረቢያ ዝርዝር “አንድኦርጅናል እና ኮፒ” በድምሩ ሁለት ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እንዲሁም የድርጅቱ ስም፣አድራሻ እና ማህተም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት በየሎቱ በመጻፍ በተናጠል በታሸገ በኤንቨሎፕ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ከቀኑ በ7 ፡30 ሰዓት ድረስ ፒያሣ እናት ህንፃ በአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  6. ጨረታው በዚያነ ዕለት ከቀኑ በ 7 ፡ 30 ሰዓት ታሽጎ ልክ ከቀኑ 8 ፡ 00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላውን ዋጋ 2% በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይምሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
  9. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካልያሳይዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተእታ/ቫት/ ጨምሮ ወይም ተእታ/ቫት በፊት መሆኑን ገልጾ መጻፍ ይጠበቅባቸዋል።ያልተገለፁ ከሆነ ተእታ/ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደረጎ ይወሰዳል።
  11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለጸው መሰረት ለተጫረተበት ዕቃ ናሙና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማቅረብ ይኖርበታል።
  12. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-126-71-02 ወይም 011-126-71-01 መጠየቅ ይቻላል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን

የአራዳ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ ጽ/ ቤት

 

 




___________________________________________________________________________________

Category : Computer and Accessories, Computer Purchase, Electrical and Electronics, Electrical Equipment and Accessories, Energy, Generators, Food and Beverage, Food Items Supply, Furnishing and Fixture, Carpets and Curtains, Partition Related, Installation and Maintenance, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Stationery Supplies, Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Purchase., Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing

Posted Date : አዲስ ዘመን ሐሙስ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ . ም  

Deadline : 2020-03-25[መጋቢት 16]

__________________________________________________________

ጽ/ቤቱ የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣የፅዳት ዕቃዎች፣ልዩ ልዩ ቋሚ አላቂ እቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ፣የህትመት ስራዎች ፣ቋሚ ዕቃዎች ፣የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች እና የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ማሽን መለዋወጫ ግዥ ለዓመት የሚቆይ ፣የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ለ1 ዓመት የሚቆይ ፣የተለያዩ የመኪና ዲኮሬሽን ዕቃዎችና ንጣፍ ስራ ፣ የፓርቲሽን ስራ ፣የባሊኮኒ/ካውንተር /conter/ ጠረጴዛ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል |በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ|

 Deadline : 2020-03-22 [መጋቢት 13]

ጤና ጣቢያው የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ የጥገና እቃዎችና ጥገና፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ህትመት፣ እንዲሁም ቋሚ እቃ ግዢ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል |በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 12 ጤና ጣቢያ| 

 Deadline : 2020-03-22 [መጋቢት 12]

ባንኩ የባንክ ቅጾች ህትመት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ |የኢትዮጵያ ልማት ባንክ | 

Deadline : 2020-03-31[መጋቢት 22]

ኤጀንሲው ከታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል |የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ |

Deadline : 2020-03-22 [መጋቢት 12]

Back to Home

Report Page