walia tender
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የኢ/ትብብር መምሪያ የመርሀቤቴ ወረዳ/ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ለሶስተኛ ጊዜ የፈርኒቸር ውጤቶችን በግልፅ ጨረታ አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እያገስፅን ።
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር ኮፒውን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- የሞሉት ዋጋ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በብር 50( ሃምሳ ብር ብቻ) ጨረታው ከወጣበት ቀን እስከ 15 ኛው ቀን 11 ፡30 ድረስ ባሉት የካላንደር ቀናት ውስጥ ከቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የሽያጭ ጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ( ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤታችን የውስጥ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ዋናውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመ/ወ/ገ/ኢ/ትብብር ዋና ጽ/ቤት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3 ፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ16 ኛው ቀን በ3 ፡01 ሰኣት ታሽጐ በ3 ፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር - 011-13-20-136/005 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም ህዝባዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የሰሜን ሸዋ ዞን
የመርሐቤቴ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ ቤት
___________________________________________________________________________________
Category : Furnitures, Office Furniture, Purchase.
Posted Date : አዲስ ዘመን ሰኞ መጋቢት 7 ቀን 2012
Deadline : 2020-03-31[መጋቢት22]
______________________________________________
ጤና ጣቢያው አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃ፣ የደንብ ልብስ እና ስፌት፣ ቋሚ እቃዎች፣ ህትመቶች፣የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ የህክምና ዕቃዎች፣ መድኃኒቶችና አዲስ የሚገጠሙ ወንበሮች እና ጥገና የሚደረግላቸው ወንበሮች ጠረጴዛ ፋይል ካቢኔቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል |የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 ጤና ጣቢያ |
Deadline :2020-03-27 [መጋቢት 18]
ጽ/ቤቱ የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣የፅዳት ዕቃዎች፣ልዩ ልዩ ቋሚ አላቂ እቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ፣የህትመት ስራዎች ፣ቋሚ ዕቃዎች ፣የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች እና የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ማሽን መለዋወጫ ግዥ ለዓመት የሚቆይ ፣የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ለ1 ዓመት የሚቆይ ፣የተለያዩ የመኪና ዲኮሬሽን ዕቃዎችና ንጣፍ ስራ ፣ የፓርቲሽን ስራ ፣የባሊኮኒ/ካውንተር /conter/ ጠረጴዛ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል |በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ|
Deadline : 2020-03-22 [መጋቢት 13]