walia tender
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ አቶ ልደት ታምሩ እና በፍ/ባለዕዳ ጃሎንግ ኮንስትራክሽን ሃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 206678 በ9/6/2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወ/12 ቶኩማ የመኪና ማቆሚያ ግቢ የሚገኝ የሰ/ቀ-3- 65807 አ.አ የሆነ መኪና የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 300,000 ( ሶስት መቶ ሺ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 1 ቀን 2012 ዓ. ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ8 ፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3 ፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ
አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
___________________________________________________________________________________
Category : Foreclosure., Vehicle Foreclosure, Sale., Vehicle and Spare Parts, Vehicle Sale
Posted Date : አዲስ ዘመን ሰኞ መጋቢት 7 ቀን 2012
Deadline : 2020-04-09[ሚያዝያ1]
____________________________________
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 7 የቤቁ አዲስ ውስጥ የሚገኝ ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 307,360.00 መሆኑ ታውቆ ሚያዝያ 15 ቀን 2012 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡|የኢፌ.ዲሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት|
Deadline :2020-04-23 [ሚያዝያ 15]
የመኖሪያ ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ|በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት|
Deadline : 2020-04-16 [ሚያዝያ 8]
በን/ስ/ላ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የቤት ቁጥር … የሆነው ቤት የቦታው ስፋት 345 ካሜ የተመዘገበ ካርታ ያለው የሆነ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 339,184.80 መሆኑ ታውቆ ለሚያዚያ 12 ቀን 2012 ዓም በሐራጅ ይሸጣል፡፡| በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት|
Deadline : 2020-04-20 [ሚያዝያ 12]