Walia tender

Walia tender

አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)March 19, 2020

2012 

ዓባይ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን እንዲሁም የተሸከርካሪ ጎማዎችን እና መለዋወጫዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: 

  1. ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች (ፕሪንተር፣ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ፋክስ ማሽን፣ ስካነር እና ኤሌትሪካል ካልኩሌተር) 
  2. የተለያየ መጠን ያላቸው የብር መቁጠሪያ ማሽኖች 
  3. የተለያየ አይነት ፈርኒቸሮች (ወንበሮች እና ፋይል ካብኔቶች) 
  4. የተሸከርካሪ ጎማዎች እና የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች 

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ህጋዊ ተጫራቾች:

ተጫራቾች ለአንድ የእቃ አይነት በአሃዝና በፊደል በመግለጽ ጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መነሻ ዋጋ መሰረት ጥቅል ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን በማካተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: 

  • የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በደብዳቤ በተገለጸለት በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለባንኩ ሂሳቡን ገቢ በማድረግ ንብረቶችን አጠቃሎ ማንሳት ይኖርበታል:: ይህ የማይሆን ከሆነ አሸናፊው ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል:: 
  • ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከዋናው መ/ቤት ግዥና ፋሲሊቲ ዳይሬክቶሬት ብር 100 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላል:: 
  • ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ለጨረታ ከሚያቀርቡት ዋጋ 20% /ሃያ በመቶ/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ለባንኩ ማቅረብ ይኖርባቸዋል : 
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት በባንኩ ዋና መ/ቤት ባንቢስ ኖክ ማደያ ፊት ለፊት ዝቋላ ኮምፕሌክስ 8ኛ ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን መስገባት አለባቸው:: ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ9፡00 ሰዓት ይከፈታል:: 
  • ተጫራቾች ንብረቶች በሚገኙበት አድራሻ ቃሊቲ ሸዋ ዳቦ መኖ ማደራጃ ጀርባ ባለው የባንኩ የንብረት ማስቀመጫ ቦታ በመቅረብ ጨረታው ከመዘጋቱ ከሶስት (3) የስራ ቀናት ቀደም ብሎ የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ መመልከት ይችላሉ:: ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::                   
  • ለበለጠ መረጃ :-ስ.ቁ. -0115549741/0115571529 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ

 

 _______________________

Categories :Banking Equipment and Services Electrical, Electromechanical and Electronics Furniture and Furnishing Office Supplies and Services Sales, Disposals and Foreclosure Spare Parts and Car Decoration Materials Wood and Wood Working

Posted date:ሪፖርተር መጋቢት 6 ቀን 2012

Dead line: March 30, 2012[መጋቢት 21]

___________________________

ድርጅቱ የሺናይደር ሥሪት የኤሌክትሪክ እቃዎች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል |ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክስዮን ማህበር|

Deadline :2020-03-24 [መጋቢት 15]

ጽ/ቤቱ የእንጨት እና የብረት ውጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ |የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ፋይናንስ ጽ/ቤት| 

Deadline : 2020-03-25 [መጋቢት 16]

Back to home

©ibex procurement solution p.l.c


Report Page