walia tender
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ፋ/ጽ/ቤት የግሬጽ ጨረታ ቁጥር 10/2012 በጀት ዓመት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ፋ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ያገለገሉ የሚወገዱ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የእንጨት እና የብረት ውጤቶች
- የእንጨት ጠረጴዛ ትልቁ
- የኃላፊ ወንበር የሌዘር
- የፈጻሚ ወንበር
- የፀሐፊ ወንበር ተሽከርካሪ
- ሼልፍ ባለመስታወት ትልቁ
- ሼልፍ ትንሹ
- ሼልፍ መካከለኛ
- የእንጨት መደርደሪያ
- ላተራራ የብረት
- ፋይል ካቢኔት ባለአራት/4/ መሳቢያ
- የእንግዳ ወንበር የእንጨት
- የእንግዳ ወንበር ባለብረት መደገፊያ
- አሮጌ ቆርቆሮ
- ጠረጴዛ ኤምዲፍ
ስለሆነም
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ፋ/ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል መወሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ሀ/በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ለ/በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት የተመዘገበ ሐ/በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ መ/TIN ነምበር ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1 ፣ ብር 5000 / አምስት ሺ/ ብር CPO በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር / ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ፋይናንስ ጽ/ቤት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዋናውና ኮፒ ማስገባት አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በ10 ኛው ቀን 8 ፡00 ሰዓት ይታሸጋል በሚቀጥለው ቀን 8 ፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ጽ/ቤቱ እስከ 20% መጨመር ወይም ቀንሶ የመሸጥ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት ከወረዳ 3 ፋይናንስ ጽ/ቤት ግቢ በሶስት ቀን ውስጥ ማውጣት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ10 ኛው የስራ ቀን 8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው ሳጥን በሚቀጥለው ቀን በ8 ፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 3 ፋይናንስ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ::
- አሸናፊ ድርጅት ውል ከፈረመ በኋላ በተገለጸው ቀን መሰረት ከግቢ ማውጣት ካልቻለ እና ያለፈባቸው እቃዎች በ3 /ሶስት/ ቀን ውስጥ ማውጣት ካልቻለ ያስያዙት CPO በመውረስ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ፋይናንስ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ለሚመለከተው አካል የጥፋተኝነት ደብዳቤ የምንጽፍ መሆኑ እናሳውቃለን ::
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ለሌላ ድርጅት አሳልፎ መስጠት አይችልም ::
አድራሻ:- አብነት አደባባይ ወደ ጦር ኃይሎች በሚወስደው መንገድ ዝቅ ብሎ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0112759102 ፣ 0112136263
የልደታ ክ/ ከተማ ወረዳ 3 ፋይናንስ ጽ/ ቤት
___________________________________________________________________________________
Category : Furnitures, Office Furniture, Other Furniture, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Sale., Steel/ Metals and Aluminium, Steels/ Irons and Metals, Wood and Wood Related
Posted Date : አዲስ ዘመን ሰኞ መጋቢት 7 ቀን 2012
Deadline : 2020-03-25 [መጋቢት 16]