Agri 2

Agri 2


ንብ ማንቢያ ቀፎዎችና የተለያዩ

ደንብ ማንቢያ ቁሳቁሶች ግዥ

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 082/012

የደቡብ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ የንብ ማንቢያ ቀፎዎችና የተለያዩ የንብ ማንቢያ ቁሳቁሶች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በንግድ ዘርፋ የታደሰ ፈቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 10000 ብር የጨረታ ማስ ከበሪያ በሲፒኦ ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፣
ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ከቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 30 መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛ ቀን ከቀኑ 9 ፡00 ሰዓት ድረስ የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቴክኒካ ሉን ቴክኒካል ሰነድ ፋይናንሻሉን ፋይናንሻል ሰነድ በማለት እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና CPO በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክሜንት ውስጥ በማድረግ በቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ቢሮ ቁጥር 10 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡
የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ኛው ቀን ከቀኑ 9 ፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 9 ፡05 ሰዓት ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥ ፋይ/ ንብአስ/ ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15 ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመክፈቱ ሥነ- ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡፡
ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 0462121716

በደቡብ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ

ሀዋሳ



_______________________________
Category : Agriculture, Agricultural Raw Material and Supplies, Purchase.
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 11 ቀን 2012
Deadline :2020-04-03

back to Agriculture

back to home

Report Page