ዘመድኩን በቀለ ማን ነው?ይሄ ሰው ዓላማው ምንድን ነው?ለምንስ ይሄን ያደርጋል?በሥላሴ ባሮች የተላለፈበት የእግዚአብሔር ፍርድ ምንድን ነው?

ዘመድኩን በቀለ ማን ነው?ይሄ ሰው ዓላማው ምንድን ነው?ለምንስ ይሄን ያደርጋል?በሥላሴ ባሮች የተላለፈበት የእግዚአብሔር ፍርድ ምንድን ነው?

Yenesew

🟩 🟨 🟥 የተሟላ መረዳት እንዲኖረዎ ሙሉውን ጨርሰው በደንብ ያንብቡት።

📌 ዛሬ ወገኖቼ አንድ በቴሌቪዥን መስኮት ላይ መረጃ ቲቪ በሚል ላይ የተከሰተና መምህር ነንን የሚል ነው ይህ ግለሰብ በ17/7/13 ዓ.ም የተናገረውን እጅግ ነውረኛ ውሸትን እንደ እውነት ስሎና አስመስሎ ሲሰብክና ሲሳደብ በእውነቱ ለብዙዎች ህሌና ላላቸው እጅግ እሚያም ነው።ዱርየ ፣ሌባ ወ.ዘ.ተ የሚሉ ስድቦችን ሁሉ ከአፍ ሲያወጣ ስንሰማ ጠንቋዎች ፣መተተኛዎች ሲለን እንዲሁ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ለማሳሳት በየቦታው ብቅ ካሉ ጋራ ከብዙዎች ጋራ እየደመረን እየደመረን እየደመረን ሲረግጠን ሲያነሳን ሲያብጠለጥለን በእርግጥ ብዙዎች እንደ ምትበሳጩ ቢገባኝም መናደድ መበሳጨት አይገባም።በፍጹም አይገባንም ወገኖቼ የዲያብሎስ ትልቁ መሳሪያው ውሸትን :ሲያልፍም ሰዎችን ያበሳጫል ክፉ ያናግራል የሚለውን ኃይለ ቃል ሁሉ መናገር ነው።በዚህ ሰው ላይ አድሮ የሚናገረው መንፈስ ለእኛ እንደሚገባን እንደምንረዳው ያው ሁሉም የሚያውቀው ጠላታችን ዲያብሎስ ነው።ተግባሩ ነው ለእኛ ሚሰማን ለእኛ ሚሰማን ተግባሩ ነው።ፈቅደው ወደው ለተገዙለት ሰዎች በላያቸው አድሮ ቅኖችን መልካሞችን መንቀፍ :መሳደብ :መተቸት:መክሰስ :ማዋረድ :ማፌዝ ምግባሩ ነው።ስለግለሰቡ ስብዕና ይህ ሰው ማን ነው?ለሚለው እኛ ባይገደንም በእውነት ነው የምላችሁ ባይገደንም ምንም ይሁን ምን ግለሰቡ ግለሰብ ነው።ሕይወቱም የራሱ ሕይወት ነው።ስብዕናውም የራሱ ስብዕና ነው።በጭፍን ለሚከተሉት ግን አንዳንድ ጊዜ እውነቱን መግለጽ ማስረጃዎቹን ደግሞ ምልክት መስጠት እነዚያን ተከትለው እውነቱን መፈለግ ዝም ብለው ለሚከተሉት ይጠቅማቸዋል።

እኛን ስለከሰሰ :እኛን ስለወነጀለ :በእኛ ላይ ብዙ የሀሰት ክሶች ስለደረደረ ሳይሆን ማነው? ከምን ዓላማ ነው የተነሳው?ለምን ይህንን ያረጋል? ምንድን ነው መንስኤው? ምንድን ነው ምክንያቱ ? ብሎ ሰዎች እንዲያስተውሉ ይረዳል።

በንጽጽር ቻናል ላይ የራዕይ ዮሐንስ ፳ የንጽጽር ቻናል ላይ አንዳንድ ተጨባጭ የሆኑ ስለእሱ የሚገልፁ :ስብዕናውን የሚገልፁ አንዳንድ ነገሮች ነው ተለቀዋል።መልካም ነው ከዚያ መነሻ ተነስታችሁ ይህ ሰው ሕይወቱ ምን ይመስላል?ለምን ይህን አለ?ዛሬስ ለምን ይህን ድርጊት ይፈፅማል ብሎ ለማወቅ ለመረዳት ይረዳል።ከዚያ ውጭ ራሱ ቢፀፀት ጥፋቱን ቢያውቅ መልካም ነው።

ከመስመር ወጦ ግን እጅግ በከፋ ሁኔታ በትዕቢት ተሞልቶ :በትዕቢት እኔ ነኝ ከሁሉ በላይ ማንም እኔን ሊናገር አይችልም ።እኔ የምናገረው ሁሉ እውነት ነው።ከእኔ በላይ እውነት ገላጭ የለም።በፖለቲካውም እኔ ነኝ ተንታኙ ፣በእምነቱም እኔ ነኝ ጠበቃው በሁሉ ም እኔ ነኝ ያለሁት ከእኔ አንዲት ጉድፍ ብታወጣ ወዮልህ ! አንድ ነገር እንዳተነፍስ ብቻ ዝም ብለህ ስማ የሚል ሚፎክር። እርግጥ ነው የሰለጠነ ምላስ አለ እንዳልኳችሁ ነው በላዩ ላይ የሚያድር መንፈስ ብዙ ትጥቅ ያስታጥቃል ርኩስ መንፈስ በዕውቀት የበለፀገ ነው።በጥበብ የተሞላ ነው።ይህ ትጥቁ አልተነጠቀበትም ኃይል ነው እንጅ ያጣው።

ይህ ግለሰብ ትናንትና በዘመነ ወያኔ ያው ወያኔ-1 እንበለው ያለፈውን ዛሬ ደግሞ ያለውን ወያኔ-2 ልንለው እንችላለን ከእነበረከት ስምኦን ጋራ አብሮ መስራቱን የሚያሳይ ሁሉ እያየን ነው።

#እ ቲያንሲ ምናምን የሚባል የቻይና ኩባያ አሻሻጭም እንደነበር የተመለከትነው ነው ።ዕድገቱም ከባህታዊ ገብረ መስቀል ስር እንደነበረ እየሰማን ነው ይሁን።ስለገንዘብ ፍቅር ምን ያህል ራሱንም እንዳሳለፈ ሰምተናል ይሁን ።ይህ የግለሰቡ ሕይወት ነው።በፈለገው መንገድ ይምጣ ግን ዛሬ በምን መንገድ ላይ ነው ያለው?

#እኛ ወገኖቼ በሚገባ ምናውቅና ምንረዳ ነንን አንዱ የደህንነት ክንፍ ሁኖ እየሰራ እንዳለ ግን ይገባናል።በተለይም በቤተክርስቲያን አናት ላይ ተዋቅረው እስከ ስር ድረስ የደህንነት መረብ ዘርግተው የስብከተ ወንጌሉን ፣የአስተዳደሩን ፣የፋይናሱን፣የልማቱን፣የውጭ ግንኙነቱን ሁሉ ጨብጠው የሚቆጣጠሩት ካባ የለበሱ ሰላዮች: የደህንነት ሰራተኛዎች ያሰማሩት በስውርም የሚከፍሉት እንደሆነ እኛ በሚገባ እናውቃለን።

📌እንግዲህ ብዙ ክሶች በእኛ ላይ ተሰንዝረዋል :-

🟢 .አዲስ ሃይማኖት ነው።

🟡 .አትቁረቡ ሥጋወ ደሙ አትቀበሉ ይላሉ።

🔴.ካህናትን ጥሉ ይላሉ።

🟢 .ከቤተክርስቲያን ውጡ ይላሉ።

🟡 .ፓስፖርት ያዙ መታወቂያዎች ያዙ ይላሉ።

🔴.ባንዲራ ለጥፉ ይላሉ ይህንንም ሲያደርጉ ደግሞ ለኦነግ ሊያስፈጁ ያስባሉ።

🟢 .የእኛ መዳኛችን መስቀል ነው።

🟡 .የቤተክርስቲያን መጠሪያ ትዕዛዝ :መመሪያ: ትዕዛዝ አትቀበሉ ይላሉ።

🔴.ምድረ ጎረምሳዎች :ዱርየዎች:ሌባ ቴሌግራም ላይ ተሰብስበው ይላል።

🟢 .መልሶ ደግሞ መልእክቱ አለ ሚገርማችሁ ይኼ ነው መልእክታቱ ከአንድ እስከ ስምንት ትክክል ነው ስከታተለው ነበርሁ ።ውስጡ ነበርሁ መልእክት ዘጠኝ ላይ ግን ተጠልፏል።

🟡 .ገንዘብ ደግሞ እየሰበሰቡ ነው። 

🔴.ንስሐ አትግቡ ይላሉ።

📌 እና እነዚህንና የመሳሰሉትን ክሶች በእኛ ላይ ሰነዘረ ። እነዚህን ወገኖቼ ደማምረን ወደ ዝርዝሩ ከመሄዳችን በፊት በቃሉ ጋር ከሚተላለፈው እውነት ጋር እነዚህን ክሶች በሙሉ መዝኑአቸው፣መልእክቶችን እዩ ፣ቃሎችን እዩ፣ትምህርቶችን እዩ፣መግለጫዎችን እዩ፣ሁሉንም መዝኑና እነዚህ ሁሉ ነገሮች ምን እንደሆኑ በእምነት አይን መዝኑ ።

📌.እኛ አዲስ ሃይማኖት የለንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልጆች ነንን።ያንኑ የአባቶቻችንን ሕግ ይዘን ነው ምንቀጥለው ።አትቁረቡ ሥጋወ ደሙ አትቀበሉ ብለንም አናውቅም አንልምም ውግዘቱን ግን እወቁ: አስተውሉ ብለናል።ከውግዘቱ ነፃ የወጣ ይህንን የተረዳ ካህን፣ዲያቆን አገልግሎቱ ባለበት ሁሉ ይህንን ፈፅሙ ብለናል።የእኛ ቤተሰቦች ናቸው እንዲያውም በአግባቡ ይኼንን እየፈፀሙ ያሉት።

📌.ካህናትን ጥሉ አላልንም እንዴት ካህናትን እንጠላለን በእውነትና በትክክል እግዚአብሔርን እያገለገሉ ያሉ ካህናትን አንጠላም። እንወዳለን :እናከብራለን በእነሱም እንባርካለን ከእነሱም ንስሐ እንወስዳለን ወደ እግዚአብሔርም ቀርበን ንስሐችንን እናራግፋለን።

📌ከቤተክርስቲያን ውጡ? ውጡ ሚሉት እነሱ ልበ በሉ ወገኖቼ ይህንን እኔ ስናገር እናንተ ናችሁ በእናንተው ላይ የሚፈፀም ስለሆነ የምታስተውሉ እናንተ ናችሁ። ከቤተክርስቲያን ውጡ ከቤተክርስቲያን ተገንጠሉ ብለንም ተናግረንም አናውቅም። ውጡ የሚሉት እነሱ: ፖሊስ ይዘው መጠው የሚያባርሩ እነሱ:ይኼን ሁሉ ሚሰሩ እነሱ ናቸው

📌ፓስርት ያዙ እኛ ፓስፖርት ሚባል አላልንም ግን ከፓስፖርት አያንስም ወደ ፊት የእኛ መታወቂያ የወሰዱ ሰዎች ለአገልግሎት ሲወጡ ከፓስፖርት አያንስም የሚል ክብር ሰጠናል ነውም ደግሞ።መታወቂያ የያዘ የእኛ አባል በሙሉ ለአገልግሎት የሚጠቅመው ነው ወደ ፊት በትንሳኤው ዘመን:በሽግግሩ የትንሳኤ ዘመን በዋናውም የትንሳኤ ዘመን ሚጠቀምበት ነው።ሰጠናል ለአገልግሎት የወደድናቸውን የፈቀድናቸውን ።እየገነባን እኮ ያለነው እውነትን ነው።እየገነባን እኮ ያለነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የፈረሰውን ቅጥሯን ነው።እየገነባን ያለነው።የሚገነባው ደግሞ በእውነተኛ ልጆቿ ነው።በሌባ አይገነባም።ሲያፈርሳት የኖረ ሰው መልሶ አይገነባትም ።

📌የእኛ መዳኛችን መስቀል ነው አወ እኛስ ምናችን ነው አልን።መስቀልን እኮ መናፍቅም ደረቱ ላይ አንጠልጥሎታል ካቶሊኩም እኮ አርጎታል።

🟢 የሚለየው ግን እኛ በመስቀሉ ኃይል የምናምን

🟡 የቃልኪዳን ልጆች:

🔴የኢትዮጵያ ልጆች፣

🟢 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዶግማዋን ቅኖኗዋን ጠብቀን የምንጓዝ :

🟡 የተገባልንን ቃልኪዳን ምናከብር የምናምን:

🔴በኢትዮጵያ ትንሳኤ ፀንተን የቆምን ነንን።ይኼ ነው።

📌እኛ እኮ እውነትን ነው ምንናገረው። ሌባ ዱርየ ምናምን ይኼ ሁሉ ስድብ መተተኛ ጠንቋይ ለፍላፊ ምናምን ብዙ ተብለናል እግዚአብሔር ይስጥልን ስለነቀፋው ስለትችቱ ።ወንድሜ አንተ ስለረገምከን አንተ ስለጠላሃን አንተ ስለአጥላላሃን አይደለም እግዚአብሔር ልቦና ይስጥህ።

📌ከዚህ ክፉ እግዚአብሔር ያውጣህ ምክንያቱም ወደ በስተመጨረሻ ምንወስነው ወሳኔ አለጥርጥር በአንተ ላይ ተፈፃሚ ስለሚሆን ቀድሞ ንስሐ ዕድል ይስጥህ።ነፍስህ ከመጥፋት በትዕቢት ተሞልተህ ከምትናገረው ነገር እግዚአብሔር ልብ ሰጦ ይመልስህ።ይህንን ምላስ ይህንን ንግግር ምናለ ለበጎ ብታውለው ምናለ በቅንነትና በመልካምነት በትህትና ዝቅ ብለህ እግዚአብሔርን ብታገለግለው ምንኛ በተጠቀምህ ነበር።ሚያሳዝነንን ይኼ ነው።

📌ቀጥለህ መልእክት ዘጠኝ ላይ ግን ተጠልፏል የሚል ቃል ተናግረሃል።ያስቃል ያስገርማልም ምንድን ነው ሚጠለፈው?

 🟢 ከመልእክት አንድ እስከ ዘጠኝ የወጣው መልእክት ሁሉ የተላለፈው ይኸው ዛሬ እኔ በድምጽ በምናገረው ሰው ነው አንድ እውነት።

🟡 ሁለተኛ የተጻፈውም የተዘጋጀውም እግዚአብሔር በሰጠኝ ትዕዛዝ መሠረት እኔ ነኝ።

🔴ፊርማውም የእኔው ነው።ቃሉም ድምፁም የእኔ ነው።

📌እኛ እኮ ተገልጠን ለሰው እኮ ለመታየት ያልፈለግነው ሰውን ላለማሰናከል :ሰው ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ሰውን ነውና ሚከተለው እኛ ወደ እኛ ማምለክ እንዳይመጣ :እኛን ወደ መፈለግ እንዳይመጣ :መፍትሔ ያለው ከእግዚአብሔር እንጅ ከእኛ እንዳልሆነ እኛ ዕቃ እንደሆንን: እኛ ምናምንቴ የተናቅን ሰዎች እንደሆንን ተረድቶ እውነቱን ብቻ ጨብጦ እንዲሄድ ነው። ተደብቀው ተወትፎ ብዙ ስም ይሰጠናል እኛ መሠረታችን ይሄ ብቻ ነው።እግዚአብሔር በፈቀደ ጊዜ ደግሞ ሁሉ ይገለጣል።

ዛሬም እኮ እግዚአብሔር ስለፈቀደ ነው አንተ በቴሌቭዥን ላይ መጠህ ስለእኛ የተናከርከው እግዚአብሔር ባይፈቅድ አትናገርም ነበር።ፈቃዱ የእግዚአብሔር ነው ስለአላወቅከው እንጅ ወንድሜ።

ሰው እንዲሰማ ያልሰማ እንዲሰማው ስለእኛ እንዲያውቅ ።ምናለ ይላል የእግዚአብሔር ቃል አባቶቻችን ሲናገሩ ምናለ የእግዚአብሔር ስም በክፉዎችም በክፉ ቢነሳ እ የመድኃኔዓለም ስም በክፉዎችም ቢነሳም ምናለ አምላኬ ስሙ ተሰበከ ተነገረ እንጅ ነው ያለው ጳውሎስ ሐዋርያው።እኛ ምናምንቴዎች አንተ ስለአነሳህ ብዙ ሰው ማን ናቸው :ማን ናቸው እያለ አወቀን።ራዕይ ዮሐንስ 20 ምንድን ነው?በውስጡ ምን አለ ሰው አወቀ።ድሮ ምንም ጆሮ ያልሰጠው ዛሬ ብዙ ህዝብ ጆሮ እየሰጠ ነው።አልተረዳህም እንዴ በመላው ዓለም ላይ እኮ ከመቶ ቋንቋ በላይ እኮ ተተርጉሞ መልእክታቱ ሁሉ ተበትኗል።ግድ ኢትዮጵያ ብቻ ነው እንዴ ያለው?አይደለም እኛ እየውልህ እዚህ ቁጭ ብለን :እዚቺው ኢትዮጵያ ተቀምጠን በመላው ዓለም መልእክቱ ለሁሉ አዳም ዘር እየሄደ ነው።ደርሷል ማንም አያቆመውም።ሁሉም ጆሮ ገባ ዛሬ ደግሞ በቴሌቪዥን አወጅኸው እግዚአብሔር ይስጥልን እናመሰግናለን።

ውስጡ ገብተን ተከታትለነዋል ተከታተል በጣም ደስ እሚል ነው እውነቱን ታውቀዋለህ ህሌናህ ያውቃል።እውነትን ታውቃለህ አየህ አየህ ከአንድ እስከ ስምንት የተነገረው እውነት ነው ብለህ በአፍህ መስክረሃል።በአፍህ መስክረሃል ዘጠኝ ላይ ተጠልፎአል ምንም ጠላፊ የለም።ሚጠልፈንም የለም ማንም ሊጠልፈን አይችልም።እኛው ነንን እኛው የእግዚአብሔር ባሮች ነንን።

📌ስለገንዘብ እኛ በድካማችን የምንኖር ሰዎች ነንን አቅማችን በፈቀደ ልክ በዚያው እየለፋን የምንኖር ነንን።የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ደግሞ ቢደጋገፉ በገንዘብም በሃሳብም በወንድማማችነትም ቢያደርጉ መብታቸው ነው።አንተ ኦዲተራችን አይደለህም ወንድሜ ።አንተን አልቀጠርንም በላያችን ላይ ተቆጣጣሪ አድርገን የሚያገባህ የለም ስለ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰብ ሕይወት የራስህን ሕይወት ተከታተል።

በአገልግሎት ላይ የተሰማሩትን አንዱ ልጃችንን አብጠልጥለኸዋል እግዚአብሔር ይመስገን ቧንቧ ሰራተኛ ምናምን ብዙ ብለኸዋል ማነህ ግን አንተ?ይኼን ያክል ለመሳደብ ድፍረት የሰጠህ ማን ስለሆንክ ነው?ይህን ያህል በትዕቢት ተገስለህ እንዲህ ምትናገር ? እንዴ ትህትና አስሮን እንጅ እኮ በሥጋ አንተ ምናችንም አይደለህም።ከጥጋችንም አትደርስም ።ስዕብናህንም እናውቀዋለን እንዲህ በትዕቢት መናገር በትዕቢት መገሰል ምንም ምንም እንደው ገንዘብ ቢከፈልህ እና ምንም ከመንግሥት ጋር ተዋቅረህ ብትሰራ እንዲህ በትዕቢት መናገር :ነገ ለሚፈርሱት አሁን የተመካህባቸው። እኛ እኮ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለነው እንዳንተ ጀርመን ውስጥ ተደብቀን አይደለም ምንናገረው እዚያ ያስቀመጡህ ሌላው ክንፍ ሁነህ እኛን ታጠቃለህ እኛ ላይ ትዘምታለህ ነውር ነው።ነውር እማ ነውሩ የአንተ ነውር ነው።አንተ ነህ ነውረኛው። አንተ ነህ ነውረኛው አስተውል ወንድሜ ።

📌የሚመጣብህ አደጋ እጅግ ብርቱ ነው ልናስፈራራህ አይደለም እውነቱን ነው የምገልፅልህ በአንተ ንግግር ሳቢያ ይኼው ከዚህ ሚከተለው ውሳኔ ተላልፏል።ከአንተ ከአንተ ይጀምርና በዘመቻው ሁሉ የተሳተፉትን አካቶ በይፋ ወጠው ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃንን ከተቹት ጀምሮ በስውር ከጀርባ ሁነው የሚያቀናብሩትን አካቶ እነሱንም በመንግሥት ኃይል ተደግፈናል የሚሉትን የትዕቢት ሰራዊቶች ሁሉ ያለውንም መንግሥት ጨምሮ ሌሎችንም አካቶ ከአንተ ከቤተሰብህ ተነስቶ ከቤተሰብህ ቃሌን ልብ ብለህ አዳምጥ ከቤተሰብህ ተነስቶ በአንተ የሚደመደም ቅጣት ወስነናል።

ይህ ደግሞ በአደባባይ ወጠው ለተቹን: ለሰደቡን :እኛን እናዋርዳለን ብለው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የተላለፈውን መልዕክት ለዘለፉ ሁሉ የሚፀና የቅጣት ውሳኔ ነው።አይሻርም አይለወጥም።

📌ፎክሩ ተቹ ምናምን ብለሃል እኛ ፎካሪ አይደለንም ።ተቺ አይደለንም ።እኛ አስፈራሪ አይደለንም ።የእግዚአብሔርን እውነት ግን ገላጮች ነንን።ይህ በተግባር በሕይወትህ ላይ ሲፈፀም ታየዋለህ በዚያ ትደመደማለህ።ቅድሚያ ግን የቤተሰብህን ጥፋት ታያለህ ቀጣይ በራስህ ይወሰናል።አንተ ላይ ይደመደማል።ሁሉም ላይ ይሄ ይወሰናል።በአንተ እርቀት አካሄድ ሌሎችም በዚህ ተካተዋል።

📌እኛ ዝም ብለን አይደለም ከመንግሥት ጋር የተዋቀርህ መሆንህን የገለጽንልህ በአጭሩ በቅርቡ በዚችው ሰሞን ዳንኤል ክብረት የሚባልን ቤተክርስቲያንን እጅግ የጎዳ ማህበረ ቅዱሳንን በሙሉ ውስጡ ሰላይ ሰግስጎ ለመንግሥት አዳሪ ያደረገ ዛሬ ደግሞ በውስጧ የበቀሉትን እሱ የመለመላቸው ሁሉ ተሰብስበው እናት ፓርቲ ይላሉ።

እኛ ስለምርጫችሁ ስለመመራረጣችሁ አይመለከተንም ይህን ሰው ምረጡ ብለህ በዚያው በገፅህ ላይ ማስታወቂያ ስሰራ ነበር። ማነህ? አየህ ማነህ? ማነህ የሚለው ራሱ ድርጊትህ መልሱን ይናገራል።ስለዚህ ውሳኔው ሲተገበር ያኔ መላው የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰብ ሁሉ እናንተ ትታዘቡንአላችሁ።እኛ ማነንን በዚህ መስመር የተሰማሩ ማን ናቸው?

📌ይህ ግለሰብ የእመቤታችን ስም አንስቶ እኔ እመቤቴን ይዤ :እኔ የቅዱሳንን ፀሎት ይዤ :እኔ አባቶች እየፀለዩልኝ ይኼ ሁሉ እየሆነልኝ ማነው ሚነካኝ እያለ ሲል ሰምታችኋል :ምስክሮች ናችሁ ።ክፉ ሲደርስ ግን : በወሰነው ውሳኔ ሲካተት ይሄ ሰው ግን የአባቶች ፀሎት አይሰራም ማለት አይደለም።የአባቶች ፀሎት ይሰራል በቅን ለሚጓዙ ያግዛል በመልካም ለሚሰማሩ ሁሉ ይረዳል።ድንግል ደግሞ መነገጃ አይደለችም  ማስፈራሪያ መፎከሪያም አይደለችም።ሰውን ወደ እውነት ምትመልስ ድንቅ እናታችን ናት። ማንም ለሥጋ ፍላጎቱ እያነሳ ሚነግድባት አይደለችም እና ነው።ስለዚህ በደፈረው ድፍረት ልክ ነው ውሳኔው የተወሰነው።

📌 እንቀጥላለን ወገኖቼ እንደገለጽነው ውሳኔአችን :ውሳኔአችን ዛሬውኑ እንዲህ ይሆናል እንዲህ ይሆናል ብለን ባንጠብቅም ሁሉን በጊዜውና በስዓቱ ስለሚፈፀም ያንን በትዕግስት እናያለን።

 📌እኒህ ሰው የሚያቀርቧቸው ብዙ ቪዲዮዎች ፎቶዎች እንዲሁ በዚህ በቴሌቪዥን ላይ ተመልክተናል።ሰዎች በኦነግ ሲረሸኑ ኦነግ ሸኔ የሚባል ህፃናት ሲታረዱ ሲፈናቀሉ ትኩሱን ድርጊት :ትኩሱን ድርጊት እረሻኞቹ የሚያቀርቡትን የሚቀርፁትን በአማራው ህዝብ ላይ የፈፀመውን ግፍ ያቀርባሉ።ላኪዎች እንግዲህ እረሻኖቹ ናቸው። በቲቪ መስኮት ሚቀርበው በእርስዎ ነው ለምን ዓላማ? አዎን በእኛ መረዳት በአሁኑ ሰዓት ያለው መንግሥት ውስጥ የተደራጀ የጠላት ኃይል ፀረ አማራ ኃይል አማራውን ያለውን ወኔ የመስበር :የኦሮሙማን ኃይል የማይቻል ነው በሚል የስነ አምዕሮ ተፅዕኖ ለመፍጠርና የተሸናፊነት ስሜት እንዲያድርበት ለማድረግ የሚከናወን ጭቃኔዊ የተሞላበት ድርጊት ነው።

በእኛ አወቁትም አላወቁትም እየሰሩ ያሉት ለዚሁ አዘንኩለት ለሚሉት አማራ መጥፋት እንደሆነ ነው ሚሰማን ምክንያቱም ይህ ድርጊት ይህ ክንዋኔ በየዕለቱ ሚገለጸው በእርስዎ ነው።በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ግን ይኼ አይነገርም።በሌሎች ሚዲያዎችም በአብዛኛው አናይም።በእርስዎ ጋር ግን እናያለን።ይህ በርግጥ እንዴት ነው እንዲህ መረጃ በትኩስ ሚፈሰው የሚለው እርግጥ ነው ስለማንነትዎ እንድንጠረጥር ያስገድደናል ከኋላዎ ታሪክዎ ጋር ስናየይዘው።

📌ሌላው የካቲት/23/2013ዓ.ም በተገለጸው አጭር መግለጫችን በሰንዳፋ በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ስም የተከናወነ አሳፋሪ ተግባር እንደተከናወነ ገልጸናል።በስማችን ማለት ነው።እኛ ማናውቀው የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በማናውቀው በአንድ ቤት ላይ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ስምን ለጥፈው ከቤተክርስቲያን ውጡ እዚህ ተጠመቁ :የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን እዚህ ታጠምቃለች: እዚህ እንዲህ ታደርጋለች : ውጡ እያሉ: ማናቃቸው: ማንረዳቸው ደህንነቶች ያቀናበሩት ሲከናወን አይተናል ሰምተናል።ይህንንም በጊዜው እኛን የሚጠሉ የእኛን ስም ለማጉደፍ የሚተጉ እንዴት እያቀናበሩ እንዳለ ለህዝቡ እንዲያውቀው በግልጽ በዕለቱ መግለጫ ሰጠናል።ይህንን ደግሞ ያከናወኑት የደህንነት ሰዎች እንደሆኑ ይህን አደራጅተው የእኛን ስም ፊልም ቀርጸው ፎቶ ቀርጸው ስማችን ለማጥፋት እንደነበረ በሚገባ ገልጸናል።ተግባራችንም እንዳልሆነ እምነታችንም አስተሳሰባችንም እንዳልሆነ ገልጸናል ።ለካ ዝግጅቱ በስተኋላ በእኛ ላይ ዘመቻ ለመክፈት እሚያግዝ ማስረጃ መሰል ቅንብር ለማከናወን የተደረገ የደህንነት ተግባር መሆኑን ዛሬ በእርስዎ አፍ ሲነገር ስለሰማን በዚህ አረጋግጠናል።ይሄ ደግሞ አንዱ ከደህንነቱ ጋር ለመስራትዎ ሌላው ማረጋገጫችን ሁኗል።

📌በዚህ ብቻ አልቆመም ቴዎድሮስ ነኝ የሚል ጫት ቃሚ: ሀሽሻም ብለው አሁን መልስ ይሰጠኛል ብለዋል ።እንዴ ጫት ቃሚ ሀሽሻም እንዲህ ሚናገር ከሆነ ሚገርም ነው።እንዲህ አይነት ስብዕናን እንጥላለን ብለው የሚሰነዝሩት ስድብ በእርግጥ ለእኔ ምንም ሚሰጠኝ ስሜት የለም ለአልሆንኩትና ለማላውቀው ድርጊት።ምን አልባት ከእርስዎ አንደበት ይሆናል እራሱ ምን እንደሆነ ይህንን ቃል ምሰማው ።አሁን መልስ ይሰጠኛል ላሉት እኔ በብስጭት በንዴት ተነስቼ እንዲህ እንዲህ ነው ምለው ነገር የለም።ስድብ :ትችት:ብዙ ዘመኖችን በሙሉ ስሰማቸው የኖርሁአቸው ናቸው ግን ለሰነፍ እንደስንፍናው መልስለት አዋቂ የሆነ እንዳይመስለው ይላል መጽሐፈ ምሳሌ ውስጥ ስለዚህ መልስ መስጠት ግድ ነው።ለዛሬው ማለት ነው ከዚህ በኋላ ለሚለፈልፉት አይደለም። ከዚህ በኋላ ስለእርስዎና መሰሎችዎ ከዚህ በኋላ መልስ መስጠት አግባብም አይሆንም።ጊዜአችንን በዚህ አናጠፋም።

መጋቢት/22/2013 ዓ.ም ከወጣው ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ትምህርት መግለጫ ክፍል-፭ ከ33 ደቂቃ እስከ 1ሰዓት ከ2 ደቂቃ ላይ የተወሰደ ።

📌መግለጫ ራዕይ ዮሐንስ 20 በድምጽ 17/07/2013 ዓ.ም የወጣ:-https://t.me/RestDingleMariyam/3942

📌 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ትምህርት አዘል መግለጫ ክፍል-፭ በድምጽ:-https://t.me/RestDingleMariyam/3922

የሥላሴ ባሮች መግለጫ ስለዘመድኩን በቀለ እዚያ ላይ ተፈጸመ።

ከዚህ ቀጥሎ መግለጫው ላይ የተገለጹትን ለማስረጃ ይሆኑ ዘንድ ሊንኮችን እየተጫኑ መመልከት ይችላሉ።

፩.ዘመድኩን በቀለ ከበረከት ስምኦን የምስክርት ወረቀት ሲቀበል የሚያሳይ ምስል:- https://t.me/RestDingleMariyam/3917

፪.ዘመድኩን በቀለ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ልቅሶ ላይ በቅርበት ይሰራ እንደነበረ የሚያሳይ በቪዲዮ :-https://t.me/RestDingleMariyam/3918

፫.ሰዎች ሲረሸኑ የሚያሳይ በገጻቸው ከሚያቀርቧቸው ትኩስ መረጃዎች ውስጥ ለአብነት የሚያሳይ ቪዲዮ:-https://t.me/RestDingleMariyam/3919

፬.ቲያንስ የሚባል የዲያብሎስ የቻይና ካምፓኒ ውስጥ ሲሰሩ እንደነበር የሚያሳይ ቪዲዮ:-https://t.me/RestDingleMariyam/3921





Report Page