#ETH

#ETH


#ደብረታቦር 

የደርብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስጋታችን አልተቀረፈም። ያለውን ሁኔታ ዩኒስቨርሲቲው እንደ ገልፀው አይደለም፤ ስጋት አለብን ብለዋል። በግቢ ውስጥ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ለቀው የሄዱ ተማሪዎች አሉ፤ እኛም የምናድረው የመማሪ ክፍል ውስጥ ነው። ሎከሮቻችን እየተሰበሩ ዝርፊያ ተፈፅሞብናል ይህ ግቢው እየገለፀ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል። ምን ባጠፋነው እንዲህ የምንቀጣው መንግስት መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ጠይቀዋል። 



በሌላ በኩል...

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ስራው ከሀሙስ ህዳር 04/03/2012 ዓ/ም ጀምሮ መቋረጡን ገልጿል፤ ሁለት ተማሪዎች ተጎድተው ህክምና ተደርጎላቸው አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉም ብሏል። ነገር ግን በማህበራዊ ሚዲያ የተማሪ ህይወት እንደጠፋ የሚናፈሠው ወሬ ሀሰት ነው፤ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰቦች በሚናፈሰው ወሬ እንዳትደናገጡ ሲል መልዕክት አስተላልፏል።


#ኦዳቡልቱም

ችግራችን ዛሬም ሳይፈታ ሜዳ ላይ እንገኛለን ሲሉ የቲክቫህ ቤተሰቦች ተናግረዋል። መንግስት ምን እስክንሆን እንደሚጠብቅ አልገባንም። ችግራችንን ይፍታልን እየጠየቅን ላለው ወደቤተሰቦቻችን ሸኙን ጥያቄም መልስ ይስጠን ብለዋል።


#ወልዲያ 

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እኛ ሜዳ ላይ ወድቀን ትምህርት ተጀምሯል፤ ነገ ሊጀመር ነው እየተባለ በየሚዲያው የሚደሰኮረው ዲስኩር አበሳጭቶናል ብለዋል። እኛ ሜዳ ላይ ነው የምንገኘው ከባለፈው ሳምንት እሁድ አንስቶ ሜዳ ላይ ነው የምንገኘው እኛ በእንዲህ ያለ ሁኔታ ላይ እያለን ትምህርት ተማሩ ማለት ተገቢ አይደለም ብለዋል። ለጥያቄያችን መልስ ይሰጠን(ወደ ቤተሰቦቻችን መሄድ እንፈልጋለን) ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት ቢደረግም መስማማት ላይ ልንደርስ አልቻልንም ብለዋል።


የወልዲያ ከተማ ቲክቫህ ቤተሰቦች...

"ሰላም ፀግሽ የወልዲያ ከተማ ነዋሪ ነኝ፤ በተፈጠረው ነገር በጣም አዝነናል። የወልዲያ ህዝብ ቁጭት ላይ ነው። ወንድም እህቶቻችን የሆኑ የግቢ ተማሪዎች ከተማ ውስጥ ስናገኛቸው የባጃጅ እየከፈልን እና እየተንከባከብናቸው እንዲረጋጉ ለማድረግ እየጣር ነው። ወልዲያ ከተማ እንግዳ ተቀባይ እንጂ የረብሻ እና መበርገጊያ ከተማ እንድትሆን አንፈልግም። እናም ለወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከጎናቸው እንደሆንን ለማሳወቅ እወዳለሁ።" 


በሌላ በኩል...

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ችግር እጃቸው ያለበት አካላት ለሕግ እንዲቀርቡ ነዋሪዎች ጠይቀዋል። በወልድያ ዩኒቨርሲቲ አጋጥሞ የነበረው የፀጥታ ችግር በማኅበረሰቡ ተቀባይነት የሌለው እንደነበርና ተጠርጣሪዎች ለሕግ እንዲቀርቡ የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች ጠይቀዋል፡፡ መንግሥት የሕግ የበላይነትን የማስከበር ግዴታውን እንዲወጣም ነው ነዋሪዎቹ ያሳሰቡት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://telegra.ph/ETH-11-17-2 (አብመድ)


ተጨማሪ መረጃ #ወልዲያዩኒቨርሲቲ፦

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በነገው ዕለት ተማሪዎቹ ትምህርት እንዲጀምሩ ወስኗል፦


#ኦዳቡልቱም

ዛሬም መፍትሄ አጥተን እየተንገላታችን እንገኛለን። የመግስት ቸለተኝነት የሚያሳፍር ነው። ደህንነታችንን ማስጠበቅ ካቃተው ወደ ቤተሰቦቻችን እንድ ንግድ ይፍቀድልን ብለዋል።


#መደወላቡ

የመደ ወላቡ ተማሪዎች ችግራችን እስካሁን አልተፈታም ምንም በማናውቀው ጉዳይ እየተንገላታን እንገኛለን። የምናድረው በመማሪ ክፍል ውስጥ ነው በመከላከያ እየተጠበቅን ነው እስከመቼ እንዲህ እንደምንቀጥል አልገባንም የመንግስት ዝምታም ግራ አጋብቶናል ብለዋል።


#ደብረብርሃን

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደገለፁት ዛሬም የጎላ ችግር ግቢ ውስጥ ባያጋጥምም ችግር ይፈጠራል በሚል ስጋት በርካታ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንደወጡ ገልፀዋል። ስጋቱ አሁንም አለ የሚሉት ተማሪዎች መንግስት መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። ዩኒቨርሲቲው አካባቢ የአንድ ተማሪ ህይወት ካለፈ በኃላ በርካታ ተማሪዎች የግጭት ስጋት በፍራት ከግቢ ወጥተዋል።


#ባህርዳር 

ስጋት ያደረባቸው የፔዳ እና ፖሊ ግቢ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጥተዋል። ወደ ቤተሰቦቻቸውም የሄዱ አንዳንድ ተማሪዎች አሉ። አሁንም በሚናፈሱ ወሬዎች ተማሪዎች ስጋት ላይ ናቸው። መንግስት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሁኔታን ካልፈጠረ ተማሪዎችን ወደ ቤተሰባቸው በሰላም መመለስ አለበት ብለዋል።


ጎንደር(ማራኪ)

ዛሬም የጎላ ችግር ባይኖርም ተማሪዎች በሚናፈሱ ወሬዎች ስጋት ወደቤተሰቦቻቸው የሄዱ አሉ። በግቢ ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ከፍተኛ የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ገልፀዋል። ውይይቶች ባለመደረጋቸው ሳቢያ ሌሎች ግቢዎች ያጋጠሙ ችግሮችም እዚህም እንዳያጋጥሙ ተማሪዎች ፈርተናል ሲሉ ገልፀዋል።


#ወሎ(ኮምቦልቻ)

ተርጋግቷል አልተረጋጋም ለማለድ የሚደብድ ሁኔታ ነው ያለው። ተማሪዎች በጭናንቀት እና በስጋት ውስጥ ነው የሚገኙት። ትምህርትም ተቋርጧል። መፍትሄ አልተገኘም እስካሁን።


#ወለጋ

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢያቸው እስካሁን የጎላ የፀጥታ መደፍረስ ችግር አለማጋጠሙን ገልፀው ነገር ግን ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት አለ መነጋገር ተችሎ ችግሮች እንዲፈቱ መክረዋል። የግቢው በር ተዘግቷል ተማሪ መውጣት እና መግባት አልቻለም ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ አስረድተዋል።


#መቱ

ዛሬ ወደ ዶርማቹ ትገባላችሁ ተብለን የነበር ቢሆንም ይኸው ዛሬም ሳንገባ ቀርተናል። ችግራችን እስካሁን አልተፈታም። የተማሪው ጥያቄ ወደቤተሰብ መመለስ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዳይሄዱ አድርጓል። መንግስት እንዲህ ስንሰቃይ ለምን ይሄን ያህል ዝም እንደሚል እና አስቸኳይ መፍትሄ መስጠት እንዳቃተው ግራ ተጋብተናል ብለዋል።


የመቱ ከተማ ነዋሪዎች...

እኛ እያለን ይህ ዩኒቨርስቲ አይዘጋም....

የመቱ ከተማ ነዋሪዎች አሁን እየተስተዋለ ያለውን የጸጥታ መደፍረስ አስመልክቶ ከዩኒቨርስቲው የቦርድ አመራሮች፣ የዩኒቨርስቲው የማኔጅመንት አካላትና መምህራን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ በዚህ ውይይታቸውም ላይ እንደገለጹት "እኛ እያለን ይህ ዩኒቨርስቲ አይዘጋም" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በቀጣይም የዩኒቨርስቲውን ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት እንደሚሰሩ ነው ያስታወቁት፡፡


በሌላ በኩል...

በመቱ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ተማሪዎች ሞተዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዳያ የሚሰራጨው ወሬ ሀሰት መሆኑን ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።


#ደብረማርቆስ

ከትላንት ጀምሮ ስጋቶች አሉ። ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰቱ አይነት ክስተቶች እዚህም እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ተማሪው ከትምህርት ይልቅ ከዛሬ ነገ ምን ሊፈጠር ነው በሚል ስጋት ውስጥ ነው ብለውናል።


#ኢንጂባራ

በእንጂባራ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ምሽት የተኩስ ድምፅ የሰሙ ተማሪዎች ውጥረት ውስጥ መግባታቸውን ገልፀዋል። ግቢ ውስጥ ለማደር ስጋት የነበረባቸው ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ውጪ ወጥተዋል።


#ደባርቅ 

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስጋቶች ዛሬም እንዳሉና ችግሮች እንዳልተፈቱላቸው ገልፀዋል። መንግስት ተማሪው ላይ ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት ሊቆጣጠር ይገባል ብለዋል።


#ጅማ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄድ ያልቻሉ በየቤተ እምነቱ ተጠልለው ይገኛሉ። የሚሰማን ጣን ያለንበት ሁኔታ እጅግ የሚያሳዝን ነው እኛ ወደቤት መሄድ ያልቻልን ተማሪዎች ከፍተኛ እንግልት ውስጥ ወድቀናል ብለዋል። የሚሰማ አካል ካለ መፍትሄ ይስጠን በርካታ ጓደኞቻችን ግቢውን ለቀው ሄደዋል ብለዋል።


#ሀረማያ

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ካለፈው ስንት ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርት ሲቋረጥ ነበር፤ ሰሞኑን በተፈጠረው ክስተት ደግሞ ተማሪዎች የደህንነት ስጋት አጋጥሞ ከግቢ ከወጣን ቀናት ተቆጥረዋል ዞር ብሎ የሚያየን አካልም የለም ብለዋል። በየቤተ እምነቱ የተጠለልን ተማሪዎች አለን፤ ወደ ቤተሰቦቻቸውም የሄዱ ብዙ ተማሪዎች አሉ ብለዋል። ግቢው ችግሩን እየደበቀ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።


#ድሬዳው 

አንድ ወንድማችንን በሞት ካጣን በኃላ ግቢ የመቆየት ዋስትና በማጣታችን በአጥር እየዘለልን ለመውጣት ተገደናል። ዛሬም በርካታ ተማሪዎች በአጥር እየዘለሉ ወጥተዋል። ዩኒቨርሲቲው አስተዳደሮች ከፍተኛ የአሰራር ግድፈት ያለባቸው ናቸው። ሌሎች ብዙ ተማሪዎች ግቢውን በመልቀቃቸው ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጭር ብሏል ሲሉ ገልፀዋል። የከተማው ደህንነት አስተማማኝ ባለመሆኑ ስቃያችን ብዝቷል ሲሉም ገልፀዋል። በእምነት ተቋማት እንደሚገኙ የገለፁት እኙሁ ቤተሰቦቻችን ዩኒቨርሲቲው መረጃዎችን እየደበቀ ይገኛል ለተማሪዎቹ ደንታ የለውም፤ ይህን ያህል ስንሰቃይ አንድም ያነጋገረን አካል አልነበረም ሲሉ ወቅሰዋል። የምንፈልገው እቃዎቻችን ተሰጥተውን ወደ ሚፈልጉን ቤተሰቦቻችን መሄድ ብቻ ነው ብለዋል።


#አዳማ 

የASTU አብዛኛው ተማሪ በስጋት ሳቢያ ግቢውን እንደለቀቀ የገለፁልን ተማሪዎች ዛሬ ዩኒቨርስቲው ባወጣው ማስታወቂያ ከነገ ጀምሮ ትምህርት እንዲቀጥል አዟል ብለዋል። እኘፍትሄ ሳናገኝ እንዲህ እየተሳቀቅን በየትኛው አእምሮአችን እንድንማር እንደሆነ አልገባንም በዋል። መጀመሪያ መፍትሄ ይፈለግ፤ መረጃዎችን መደባበቅ አያስፈልግም ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ለህዝብ መግለፅ ያስፈልጋል ብለዋል።


#ASTU

ዛሬ ዩኒቨርሲቲው በድጋሚ ባወጣው ማስታወቂያ ነገ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀትሉ ይህን በማያደርጉት ላይ ግን እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጿል።

ሙሉ ማስታወቂያው፦


Report Page