ገነቴ ነህ

ገነቴ ነህ

Solicious18 Wallpapers™
ኢየሩሳሌም ነጊያ | ገነቴ ነህ

ባለብሰው ገላዬን አዲሱ ያረጃል

የተጫሙ እግሮቼ ሌላ ያምራቸዋል

ደግሞ ይርበዋል ያበላሁት ሆዴ

ጥሜ ቆረጠ ስል ውኃ ጠማው አፌ

የኑሮዬ ቋቱ ገደቡ ላይሞላ

ስባክን ስዳክር ብዬ እንዳልቀር ኋላ

ሰማዩን ረስቼ ምድሩን ቆንጥጬ

አብላኝ አጠጣኝ ስል ለስጋዬ ሮጬ

አይጠረቃ ሕይወቴ አይሞላ ክፍተቴ

መቼ በቃኝ ያውቃል ይኼ ማንነቴ

በምድራዊው አይደል በእህል እና ውኃ

ለካስ ኢየሱስ ነው የመንፈስ ፍስሐ

ለካስ ኢየሱስ ነው የነፍሴ ፍስሐ

የልቤ ሐሴት የውስጤ እርካታ

የሱስ አንተ ነህ የነፍሴ ፋታ

ባንተ ደስ ይለኛል ሁልጊዜ ሐሴት አደርጋለሁ

የሰጠኸኝ ደስታ ፍጹም ነው እፍለቀለቃለሁ

የልቤ ሐሴት የውስጤ እርካታ

የሱስ አንተ ነህ የነፍሴ ፋታ

ባንተ ደስ ይለኛል ሁልጊዜ ሐሴት አደርጋለሁ

የሰጠኸኝ ተስፋ ፍጹም ነው እፈነድቃለሁ

ባልበላም ጠግቤ አድራለሁ

ባልጠጣም ረክቼ ኖራለሁ

አንተ ካለህ ምን እሆናለሁ?

አንተ ካለህ ምን እሆናለሁ?

በረሀው ላይ አስቀኸኛል

ገነቴ ነህ አርክተኸኛል

ፍቅርህ ብቻ ይበቃኛል

መገኘትህ ያረካኛል

አንተ ካለህ ምን ያሻኛል?

ፊትህ ብቻ ይበቃኛል

ባልበላም ጠግቤ አድራለሁ

ባልጠጣም ረክቼ ኖራለሁ

አንተ ካለህ ምን እሆናለሁ?

አንተ ካለህ ምን እሆናለሁ?

በረሀው ላይ አስቀኸኛል

ገነቴ ነህ አርክተኸኛል

ፍቅርህ ብቻ ይበቃኛል

መገኘትህ ያረካኛል

አንተ ካለህ ምን ያሻኛል?

ፊትህ ብቻ ይበቃኛል?

ኢየሩሳሌም ነጊያ | ገነቴ ነህ


"ገነቴ ነህ" ኢየሩሳሌም ነጊያ | Official Music Video


Report Page