ይብሱን ወደድኩህ

ይብሱን ወደድኩህ

Solicious18 Wallpapers™
ህሊና ዳዊት | ይብሱን ወደድኩህ


ነፍስ እያወቅሁ ስመጣ ቀን ሲጨምር

ክፉ ደጉን መለየት ስጀምር

ዛሬ ትላንት ሲሆን ነገ ደግሞ ዛሬ

እየዋለ እያደር ጨመረብኝ ፍቅሬ

ዛሬ ትላንት ሲሆን ነገ ደግሞ ዛሬ

እየዋለ እያደር ጨመረብኝ ፍቅሬ


ወድጄሀለሁ ወድጄሀለሁ

ወድጄሀለሁ ወድጄሀለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ


ማዕበሉ ሲገፋኝ እምነቴ ገነነ

ፈተናው ሲጨምር ልቤ ሙሉ ሆነ

ስምህን የሚያስጥለኝ ሁኔታ ሲመጣ

ይብሱን ወደድኩህ ፍቅሬም ገደብ አጣ


ማዕበሉ ሲገፋኝ እምነቴ ገነነ

ፈተናው ሲጨምር ልቤ ሙሉ ሆነ

ስምህን የሚያስረሳኝ ሁኔታ ሲመጣ

ይብሱን ወደድኩህ ፍቅሬ ገደብ አጣ


በስተ መጨረሻ ሞት እርፍን ጨብጦ ሲመጣ እያየሁት

ነገሬ ሊያበቃ ሊያልቅልኝ መሆኑን ቁርጤን እያወቅሁት

ሙሉ ማንነቴን ሰጥቼ አረፍኩት

ሙሉ ማንነቴን ሰጥቼ አረፍኩት


ወድጄሀለሁ ወድጄሀለሁ

ወድጄሀለሁ ወድጄሀለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ



ድቅድቁ ጨለማ እንዳለህ ነገረኝ

ወጀቡ አንሳፍፎ አንተ ጋር አደረሰኝ

ትዕግስቴ ሲፈተን እምነቴ ሲለካ

አንተ አስመስሎ ሊሰራኝ ነው ለካ


ድቅድቁ ጨለማ እንዳለህ ነገረኝ

ወጀቡ አንሳፍፎ አንተ ጋር አደረሰኝ

ትዕግስቴ ሲፈተን እምነቴ ሲለካ

እንዲህ አሳምሮ ሊሰራኝ ነው ለካ


በስተ መጨረሻ ዙሪያው ገደል ሆኖ ልቤ ተስፋ ሲያጣ

አምላክሽ የት አለ አያይም ወይ የሚል ጥያቄ ሲመጣ

ከችግሬ ገንኖ እልልታዬ ወጣ

ከንጋቴ ቀድሞ አምልኮዬ ወጣ


ወድጄሀለሁ ወድጄሀለሁ

ወድጄሀለሁ ወድጄሀለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ

አንተን መምሰልን እንደ ማትረፊያ ቆጥሬዋለሁ


ህሊና ዳዊት | ይብሱን ወደድኩህ

💌 Nardos



ህሊና ዳዊት "ይብሱን ወደድኩህ" Official Music Video


Report Page