የጣፊያ ካንሰር

የጣፊያ ካንሰር

Dr. Tena - Bethel


🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

ካንሰር እጅግ አስከፊ በሽታ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ዛሬ የጣፊያ ካንሰርን አጠቃላይ መረጃ እንሰጣለን፡፡


ጣፊያ

የጣፊያ ካንሰር ከጣፊያ ሲሎች የሚነሳ ካንሰር ሲሆን፤ ጣፊያ ከታችኛው የጨጓራ ክፍል ጀርባ የሚገኝ የሆድ ክፍል ነው፡፡ ጣፊያ ለምግብ መፈጨት የሚረዳ ኢንዛም ያመነጫል፤ እንዲሁም የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ለመቆጣጠር የሚረዳ ሆርሞንም ያመነጫል፡፡


የጣፊያ ካንሰር

የተለያዩ ባዕድ ነገሮች ከጣፊያ ሊበቅሉ ይችላሉ፤ የካንሰር ባህሪ ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም ይችላል፡፡ በጣም የተለመደው የካንሰር አይነት ፓንክሪያቲክ ዳክታል አዴኖ ካርሲኖማ (Pancreatic Ductal Adenocarcinoma) ይባላል፡፡

የጣፊያ ቻንሰር ብዙውን ጊዜ መዳን በሚችልበት ደረጃ አይገኝም፤ አስከፊ ደረጃ ሲደርስ ነው የሚታወቀው፡፡ ምክንቱም ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ከመሰራጨቱ በፊት ምንመ አይነት ምልክት አያሳይም፡፡

ህክምናው በስርጭቱ መጠን ላይ ይወሰናል፡፡ ቀዶ ጥገና፣ ኬሞቴራፒ፣ የጨረር ህክምና ወይም እነዚህ አንድ ላይ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡


ምልክቶች

ከላይ እንደጠቀስነው ካንሰሩ ሳይሰራጭ ምልክት አያሳይም፤ ከዛ በኋላ ግን የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፤

-         ወደ ጀርባ የሚሄድ የሆድ ህመም

-         የምግብ ፍላጎት መቀነስ

-         ክብደት መቀነስ

-         የቆዳ ቢጫ መሆን

-         የሰገራ መንጣት

-         የሽንት መጥቆር

-         የቆዳ ማሳከክ

-         የነበረን የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር መቸገር ወይም የስኳር በሽተኛ ያልነበረ ሰው ላይ የስኳር በሽታ ሲገኝ

-         የደም መርጋት

-         ድካም



ሃኪሞት ጋር መቼ መሄድ አለቦት?

ለምን እንደሆነ በማታቁት መልኩ ምልክቶች ካስተዋሉ ሃኪሞትን ቢያማክሩ ይመከራል፡፡


በምን ምክንያት ይመጣል?

የጣፊያ ካንሰር በምን ምክንያት እንደሚመጣ የተረጋገጠ ምክንያት የለም፡፡ ሃኪሞች አንዳንድ ነገሮች ተጋላጭነትን እንደሚጨምሩ ታይቷል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ሲጃራ ማጨስ እና ከቤተሰብ የሚወረስ የጂን ችግር ይጠቀሳሉ፡፡


ተጋላጭነት

·        ሲጃራ ማጨስ

·        የስኳር በሽታ

·        ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የጣፊያ መቆጣት

·        በቤተሰብ የጣፊያ ካንሰር ወይም ሌሎች ለካንሰር የሚጋልጡ የጀነቲክ ችግር መኖር

·        ከልክ ያለፈ ውፍረት

·        የእድሜ መግፋት (በተለይ ከ65 ዓመት በላይ መሆን)


ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ እነዚህ ተጋላጭ የሚያደርጉ ሁኔታዎች በአንድ ላይ መገኘት (በተለይ ሲጃራ ማጨስ፣ የስኳር በሽታ እና ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ) የበለጠ ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡


ምን ሊያመጣ ይችላል?

የጣፊያ ካንሰር ቀስ በቀስ የሚብስ በሽታ ነው፤ በተያያዥነት የሚከተሉት ሊመጡ ይችላሉ፡፡

·        ክብደት መቀነስ

·        የቆዳ ቢጫ መሆን

·        የሆድ ህመም

·        የአንጀት መዘጋት


እንዴት መከላከል ይቻላል?

-         የሚከተሉት የጣፊያ ካንሰር ተጋላጭነትን ሊቀንሱ ይችላሉ፤

-         ሲጃራ ማጨስን ማቆም

-         ጤናማ የሰውነት ክብደት

-         ጤናማ አመጋገብ

 

ምርመራ

ሃኪሞ የጣፊያ ካንሰር ሊሆን ይችላል ብሎ ካሰበ የተለያዩ የደም፣ አላትራሳውንት፣ ሲቲስካን እና ሌሎች ምርመራዎችን ያዛል፡፡ የጣፊያ ካንሰር መሆኑ ከተረጋገጠ የትኛው ደረጃ ላይ እንዳለ ይለያል፤ ምክንያቱም የህክምናው አይነት ለመወሰን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡


ሕክምና

በካንሰሩ ደረጃ መሰረት የተለያዩ የህክምና አማራጮች አሉ፤ ቀዶ ጥገና፣ ኬሞ ቴራፒ እና የጨረር ህክምና ይጠቀሳሉ፡፡


በሽታው የከፋ ደረጃ ከደረሰ ግን የህክምናው አላማ ማዳን ሳይሆን ህይወት እስኪያልፍ ድረስ ህመም እንዳይሰማ ማድረግ እና ሌሎች ምልክቶችን ለማስወገድ ይሆናል፡፡


ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

                            

 ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

         የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                          t.me/DoctorTena

         የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                        fb.com/DoctorTenaEthiopia



Report Page