ኦርቶዶክሳዊ የጾታ ትምህርት   

ኦርቶዶክሳዊ የጾታ ትምህርት   

@YeBiruk ዲያቆን ቡሩክ ይርጋ ዘውብ

✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

        አሜን

ክፍል አንድ

በቃል ያለ ይረሳል፤ በጽሁፍ ያለ ይወረሳል

    ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

     ኦርቶዶክሳዊ የጾታ ትምህርት   

    ✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥  


✍መግቢያ


📌 የጾታ አጠቃላይ ትርጉም


❖ ኦርቶዶክሳዊ የጾታ ትምህርት ሲባል፣ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስለ ጾታ የሚሰጠውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት፣ ስለ ጾታ ያላትን አመለካከት፣ ቀኖናዊ ሥርዓትና ባህላዊ ትውፊት የሚያመለክት ትምህርት ማለት ነው ። 


❖ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው ጾታ የሚለው ቃል በአርአያ እግዚአብሔር ከተፈጠረው የሰው ዘር ጀምሮ፣ በመውለድ መዋለድ፣ የመብዛትንና የመባዛትን ተፈጥሮአዊ ጸጋ ከእግዚአብሔር አምላክ ያገኘ ፍጡር ሁሉ "ተባዕታይ አንስታይ " ወይም "ወንዴና ሴቴ " እየተባለ የሚጠራበት በተፈጥሮ አካል የሚለይበት ስያሜ ነው። 


❓ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ስለ ጾታ ምን ታስተምራለች


❖ የጾታ ነገር ሲነሳ የነፃነትና የእኩልነት ጥያቄ ቀዳሚ ጉዳይ ሆኖ የሚታይ የዘመኑ ዐብይ ጉዳይ ነው፤ ይሁንና ሃይማኖትን ከልማድ መለየት የተሳነው፣ የአዲሱ ዓለም አይዲዮሎጂ አራማጅ ትውልድ፣ ለጾታ ልዩነት፣ በተለይም ለሴት የመብት፣ የነፃነትና የእኩልነት መጓደል ተጠያቂ ሃይማኖት እንደሆነ ይናገራሉ።


❖ ሃይማኖት ሴትን ከሰብአዊነት በታች አድርጎ ይመለከታል፣ የሴትን ሰብአዊ ክብር ይቀንሳል እያለ ዘመናዊ ሳይንስ መስበክ ከጀመረ ሰነባብቷል፤ እውነቱና የእነሱ ፈሊጥ ፈፅሞ የተለያየ ነው።


📌 እነዚ ወገኖች ለምን በሃይማኖት ላይ መዝመትን መረጡ ቢባል


1ኛ ሰው


❖ በእንስሳዊ ባሕርዩ ልጓም በሌለበት የፍትወት ሜዳ ሽምጥ መጋለብን ይፈልጋል፤ ሃይማኖት ግን ልቅነትን ስለማይፈቅድ ሰው እንስሳዊ ባህሪውን አስወግዶ ለመንፈሳዊ ስርዓት እንዲገዛ ስለሚያስተምር ሃይማኖት አልባ ሰው በመፍጠር ዓለምን በልቅነት ለመፈንጨት እንዲመቻቸው ሲሉ 


2ኛ ሃይማኖት


❖ በተለይም ለሴት ልጅ መብትና ነፃነትና እኩልነት አያስተምርም፣ የእኩልነት ጠበቃችሁ እኔ ነኝ ብሎ ሴቶችን ሃይማኖትን እንዲጠሉ ለማድረግ


3ኛ ይህን መሰል ፈሊጥ የሚከተሉ ግለሰቦች ከሚኖራቸው አናሳ የሃይማኖት እውቀት ሌላ የመጻሕፍትን ጥሬ ቃል እንዳሻቸው በመተርጎም የተዛባ አመለካከታቸውን በቀላሉ በሚማረክ አይምሮ ላይ ያሰርፃሉ፤ ይህ ግን ስህተት ነው


✍" ... ወንድ የለም ሴት የለም ሁላችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ናችሁ እንጂ " ብሎ የጾታ እኩልነትን ያስተምራል።

📖ገላ 3፥28


❖ ተቃዋሚዎች ግን ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በፃፈው መልእክቱ ላይ


✍"ሴት በፀጥታ ትማር ፣ በፍፁም ቅንነትም ትታዘዝ፣ ሴት እንድታስተምር አንፈቅድም በወንድ ላይም አትሰልጥን በፀጥታ ትኑር እንጂ " ብሏልና ሴትን መጨቆን ነው ሲሉ ይሰማሉ።

📖1ኛ ጢሞ 2፥11


📌 በመሰረቱ ሴት በአደባባይ ወጥታ እንዳታስተምር የመባሉ ነገር


1ኛ አዳም እንዳይበላ የተከለከለውን ፍሬ በለስ እንዲበላ በማድረግ ሔዋን ምክንያተ ስህተት በመሆንዋ፣ አሁንም ምክንያተ ስህተት እንዳትሆን፣ የሴት የሥራ ድርሻ /በመንፈሳዊ ዘርፍ / ተለይቶ ተቀምጧል።


2ኛ ከሴት በፊት የተፈጠረው ወንድ በመሆኑ ባል በሚስቱ እንዲከበር የሆነው በአፈጣጠር ቀዳሚነት ስላለው ነው። 


📌 ሴቶች በቅድስና ሕይወት


❖ ቅድስና ከማንኛውም ክብር የላቀ የቤተክርስቲያናችን የክብር ሁሉ ጉልላትና ራስ ነው።


❖ በቤተክርስቲያናችን እምነትና ሥርዓት ቅድስና ለወንድ ብቻ እንጂ ለሴት አይገባም አልተባለም፤ ቅዱሳን ወንዶች የመኖራቸውን ያህል ቅዱሳን አንስት /ሴቶች አሉ፤ ይልቁንም የቅድስተ ቅዱሳንን ድንግል ማርያምን ክብርና ቅድስና ስንመለከትማ " በወንድ ምን ቅድስና አለና ነው " ወደሚል አቅጣጫ ያመጣናል።


❖ የድንግልን ያህል ባይሆንም ሌሎችም ቅዱሳን ሴቶችን ገድል ፅፋ ቤተክርስቲያን አንጻ ታከብራለች፤ በምድር ያለች የእግዚአብሔር መንግስት ምትባለው ቤተክርስቲያን የጾታን እኩልነት ምትሰብክና ምትቀበል መሆኗን አውቀው የተሳሳተ አስተሳሰብ የያዙ ሰዎች አመለካከታቸውን ያስተካክሉ ዘንድ መልእክታችን ይድረሳቸው ።


📌 አዘጋጅ

® ዲ/ን ቡሩክ ይርጋ 


✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝🔔✝


✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"

📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ


        

           ወስብሐት ለእግዚአብሔር

                  ይቆየን 



                  ይቀጥላል 

           🙏 ሼር ማድረግ አይርሱ 🙏



🕹 ትምህርቱ እንዴት ነው......የእናተ አስተያየትና ጥያቄ ከዚህ የበለጠ ለመትጋት ይረዳልና መልእክት ይተውሉኝ

 📩Coment- Telegram ላይ @YeBiruk Or #Discussion



  ─────────

  Ⓡ @Tewahedo12

 ─────────

Report Page