እንዲሁም አመሰግናለሁ

እንዲሁም አመሰግናለሁ

Solicious18 Wallpapers™
ቤተሰብ ንጎ | እንዲሁም አመሰግናለሁ

ወዳጄ ብልህ ጓደኛዬ አሀሀ

ይህም አነሰብኝ እኔስ ቀለለብኝ

አባቴ ብልህ መመኪያዬ መኩሪያዬ

ይህም አነሰብኝ እኔስ ቀለለብኝ


እናቴ ብልህ እና አጉራሼ ዳባሼ

ይህም አነሰብኝ እኔስ ቀለለብኝ

እህቴ ብልህ መካሪዬ መላሼ

ይህም አነሰብኝ እኔስ ቀለለብኝ


እንኳንስ ወዳጅም ወንድም አባት መከታ ሆነኸኝ

እንዲሁም እንዲሁም እንዲሁም አመሰግናለሁ

እንኳን የልቤን ዝምታ እንዲህ በፍቅርህ ሰብረኸው

እንዲሁም እንዲሁም እንዲሁም አመሰግናለሁ


እንኳንስ ሰበብ አግኝቼ 

እንዲሁም እንዲሁም አመሰግናለሁ

እንኳንስ ምክንያት አግኝቼ

እንዲሁም እንዲሁም አመሰግናለሁ


እንኳንስ ሰጥተኸኝ አንድ ልጅህን

ልጅህም ታዝዞልኝ ለመስቀል ሞት

በእኔ ፈንታ እርሱ ሊሞት

እንኳንስ ሽረኸው በደሌን

አስወግደኸው ኃጢአት ክሴን

በደም አጥርተህ እድፈቴን


እንዲሁም እንዲሁም እንዲሁም 

እንዲሁም አመሰግናለሁ

እንኳንስ ሰበብ አግኝቼ

እንዲሁም እንዲሁም አመሰግናለሁ


እንዲሁም እንዲሁም እንዲሁም 

እንዲሁም አመሰግናለሁ

እንኳንስ ምክንያት አግኝቼ

እንዲሁም እንዲሁም አመሰግናለሁ


ስለዳንኩበት መዳን ስላንተ ላመሰግን

ስለተወደድኩበት ፍቅር

ደግሞ በየዕለት ምህረት ሲጨመር ሌላ ምክንያት

ምስጋና እንዲሁስ ይገባህ የለም ወይ?


ባላጣም እንዲህ ሰብበ የተገባህ በመሆንህ

እንዲሁም እንዲሁም እንዲሁም አመሰግናለሁ

እንኳንስ ምህረት በዝቶልኝ በቀን ሺ ጊዜ ምረኸኝ

እንዲሁም እንዲሁም እንዲሁም አመሰግናለሁ


እንኳንስ ሰበብ አግኝቼ 

እንዲሁም እንዲሁም አመሰግናለሁ

እንኳንስ ምክንያት አግኝቼ

እንዲሁም እንዲሁም አመሰግናለሁ


ቤተሰብ ንጎ | እንዲሁም አመሰግናለሁ


ቤተሰብ ንጎ | እንዲሁም አመሰግናለሁ



Report Page