ቫይታሚን ኤ!! (Vitamin A)

ቫይታሚን ኤ!! (Vitamin A)

Dr. Tena - Bethel


🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

እንደምን ሰነበታችሁ?? 


በአዲስ መልኩ እናንተን ይጠቅማሉ የምንላቸውን የጤና ምክሮች ይዘን ተመልሰናል፡፡ በዛሬው ጥንክራችን ስለ ቫይታሚን ኤ ጉልህ የጤና ጠቀሜታ እናወራለን፤ ተከታተሉን፡፡ ሃሳብ አስተያየታችሁን በመልዕክት መላክ ትችላላቹ፡፡


ቫይታሚን ኤ እንዴት ለጤና ይጠቅማል??


ቫይታሚን ኤ ለጤና እጅግ ከፍተኛ ጥቅም ያላቸው ፋት ሶሊብል የሚባሉ ውህዶች የጋራ ስያሜ ነው፡፡ የሰውነትን ስርዓት በማሳለጥ አቻ አይገኝለትም፡፡ ከዋነኛ ጠቀሜታዎቹ መሃል እይታን ለመጠበቅ፣ የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ለማጎልበት እና የፅንስን በማህፀን ውስጥ እድገት ለማገዝ ይጠቀሳሉ፡፡


ይህ ቫይታሚን የእፅዋት እና የእንስሳት ተዋፅዕዎ በሁለት አይነት መልክ ይገኛል፤ ፕሪፎርምድ ቫይታሚን ኤ እና ፕሮቫይታሚን ኤ ይባላል፡፡ ፕሪፎርምድ የተባለው የቫይታሚን ኤ አይነት ሰውነት ሊጠቀመው የሚችለው አይነት ሲሆን የእንስሳት ተዋፅጦ ውስጥ እንደ ስጋ፣ አሳ፣ ዶሮ፣ እን የወተት ተዋፅዖ ውስጥ ይገኛል፡፡ ፕሮቫየረታሚን ኤ ከፅዋት የሚገኝ ሰውነታችን በቀጥታ ሊጠቀመው የማይችለው የቫይታሚን ኤ አይነት ነው፡፡


ፕሮቫይታሚን ኤ በሰውነታችን ውስጥ ሰውነት ሊጠቀምበት ወደሚችል አይነት ይቀየራል፤ ለምሳሌ ትንሹ አንጀት ውስጥ ቤታ ካሮቲን የተባለው የቫታሚን ኤ አይነት ወደ ሬቲናል በመለወጥ ለሰውነት ጠቀሜታ ይሰጣል፡፡


ቀጥሎ ቫታሚን ኤ ለሰውነት የሚሰጠውን ጠቀሜታ እናነሳለን፤

ቫይታሚን ኤ በምሽት ጊዜ ከሚኖርን የእይታ ችግር እና ከእድሜ ጋር ተያይዞ ከሚመጣ የእይታ መቀነስ ይጠብቃል
የአንዳንድ የካንሰር አይነቶች ተጋላጭነትን ይቀንሳል
የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ያግዛል
በብጉር የመጠቃትን መጠን እጅጉን ይቀንሳል
የአጥንትን ጤንንት ይጠብቃል
ጤናማ የሆነ እድገት እና የስነ-ተዋልዶ ጤና ለመጠበቅ ይረዳል



እናስተውል!!

ከመጠን በላይ ቫታሚን ኤ ጉዳት አለው!!

ቫታሚን ኤን ከመጠን በላይ ሲከማች ሰውነትን ሊጎዳ ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ሃይፐርቫታሚኖሲስ ኤ ይባላል፡፡ በአብዛኛው ጊዜ ቫታሚን ኤ የሚይዙ መድሃኒቶች ከመጠን በላይ ሲወሰዱ ይከሰታል፤ ከምግብ ከሚገኝ ቫታሚን ኤ ሃይፐርቫታሚኖሲስ ኤ ሲመጣ አይታይም፡፡ የሃይፐርቫይታሚኖሲስ ኤ ምልክቶች ማቅለሽለሽ፣ ማዞር፣ ራስ ምታት፣ ህመም እንዲሁም እስከ ሞት ድረስ ሊደርስ ይችላል፡፡


የትኞቹ ምግቦች ቫይታሚን ኤ አላቸው??

-   የበሬ ጉበት

-   የበግ ጉበት

-   የኮድሊቨር ዘይት

-   ሳልመን

-   ቱና

-   ቺዝ

-   ቅቤ

-   የተቀቀለ እንቁላል

-   ስ£ር ድንች

-   ካሮት

-   ቀይ ቃሪያ

-   ቅስጣ

-   ሰላጣ


ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

                            

 ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

        የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                          t.me/DoctorTena

        የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                        fb.com/DoctorTenaEthiopia


 

       



Report Page