ስንክሳር ዘሚያዚያ ፲፮

ስንክሳር ዘሚያዚያ ፲፮

@YeBiruk ዲያቆን ቡሩክ ይርጋ ዘውብ

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

       አሜን

“ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን”

(ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ)

“በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን”

(በገናና ኀይልና ሥልጣን)

“ዐሠሮ ለሰይጣን”

(ሰይጣንን ዐሰረው)

“አግአዞ ለአዳም”

(አዳምን ነጻ አወጣው)

“ሰላም” (ፍቅር አንድነት ሆነ)

“እምይእዜሰ”

(ከእንግዲህስ)

“ኮነ” (ሆነ)

“ፍሥሐ ወሰላም”

(ደስታ ሰላም)


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም


ሚያዚያ - 16 ቅዱስ አንቲቦስ ዘሃገረ በአርማ (ሐዋርያዊ ጳጳስና ሰማዕት) ዕረፍቱ ነው


  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

    ቅዱስ አንቲቦስ

  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥


❖ በዚህ ቀን ታላቁ ሐዋርያና ሰማዕት ቅዱስ አንቲቦስ ይታሰባል፤ ቅዱሱ በአርማ በምትባል ሐገር በእረኝነት (ጵጵስና) ያገለገለ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙር ነው::


❖ ቅዱሱ ስለ ክርስቶስ መንጋ ብዙ መከራን ተቀብሏል፤ በእሥር ቤት ሳለም ከቅዱስ ዮሐንስ ነባቤ መለኮት (ወንጌላዊ) ክታብ (መልእክት) ደርሶታል፤ በክታቡም ከሐዋርያትና ሰማዕታት መቆጠሩን ነግሮታል፤ ጊዜው 1ኛው ክ/ዘ ሲሆን ክታቧ ከእኛ አልደረሰችም::


❖ ከቅዱስ ዮሐንስ እግር ቁጭ ብሎ በመማሩ እንደ መምሕሩ የንጽሕና ሰው ነበር፤ ከብዙ ዓመታት አገልግሎት በኋላ ስለ ፍቅረ ክርስቶስ በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አልፏል::


❖ በታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ደግሞ የዚህ ቅዱስ ስም መጠቀሱን ምስራቅ ኦርቶዶክሶች ያምናሉ:: 


✍የእኛው (ግዕዙ) "ጻድቅየ መሃይምን" ሲለው የግሪኩ ግን በቀጥታ በስሙ "አንቲጳስ (አንቲቦስ) ብሎ ይጠራዋል፡፡

📖 ራዕይ 2፥12


❖ እርሱም በታናሽ እስያ ከነበሩት 7 አብያተ ክርስቲያናት የአንዱ (የጴርጋሞን) አለቃ የነበረ ሲሆን ሰማዕት መሆኑም በዚሁ ምዕራፍ ላይ ተጠቅሷል ፡፡


✍"በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል::


❖ የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ ሰይጣንም በሚኖርበት በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም::


❖ ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤ እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ፤ እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ::


❖ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል::

📖 ራዕይ 2፥12-17


በረከቱ ረድኤቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን


📌 ሚያዝያ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1. ቅዱስ አንቲቦስ ዘሃገረ በአርማ (ሐዋርያዊ ጳጳስና ሰማዕት)

2. ቅዱስ ሳባ ሰማዕት


📌 ወርኀዊ በዓላት

1. ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)

2. ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)

3. ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም)

4. ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ

5. አባ አቡናፍር ገዳማዊ

6. አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ

7. አባ ዳንኤል ጻድቅ


✍ "ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለእለ አነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባክያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ዓዲ ወመነኮሳት ሔራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕጻን ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘ አጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም አራቂተ ኩሉ እምባዕ ስኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይእዜ ወእስከ ለዓለም"


✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝


✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"

📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ


        ወስብሐት ለእግዚአብሔር

               ይቆየን 


  

───────────

    Channel 

 Ⓡ @Tewahedo12


       Group 

 Ⓡ @OrtodoxTewahedo12

 ───────────

Report Page