walia tender anrs edu

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EB/EMAS/06/2012
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ 5,000 ኮፒ የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት መጽሐፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊና አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
የሚታተመው የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት መጽሐፍ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 103 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% / ሁለት ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ.)ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ግብዓት ጥናትና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 6 ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16 ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና ዕሁድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ 8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቢሮ የስብስባ አዳራሽ 8:30 ሰዓት ይከፈታል::
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም
በፋክስ ቁጥር 0582201100 በመላክ ወይም
በስልክ ቁጥር፡- 0583205654 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
ባህርዳር
_______________________________
Category : Printing and Publishing., Printing and Publishing Service
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 6 ቀን 2012
Deadline :2020-03-30 [መጋቢት 21]