walia tender 13

walia tender 13


የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መ/ ቁጥር መከ/ መሐ/ ዋና መም/ ግ/ ጨ/ ቁ/09/2012

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የማቴሪያል ግዥዎች በየዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት-01 /አንድ/ ፦ ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የሲቪል ወርክ ፣ የሳኒተሪ እና የኤሌክትሪክ ማቴሪያሎች (ኳርትዝ ቀለም ፣ አጣና ፣ጣውላ ፣ ምስማርና ቆርቆሮ ፣ፒፒ አር ቧንቧ ከነፊቲንጉ፣ብሬከሮች አምፖሎች እና ኤሌክትሪክ ገመዶች)፡
ሎት-02 /ሁለት/፡- ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ቀላል ማሽነሪዎች (ኤር ኮምፕረሠር ፣ ኮንክሪት ሚከሠር ኢመርዥን ቫይብሬተርና ቶታል ስቴሽን)፡
ስለሆነም በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች፡



በሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value Added Tax) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት /ሰርተፊኬት/ ማቅረብ የሚችሉ፣
በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጨረታ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ እና በመንግስት ግዥ የግልፅ ጨረታ አፈፃፀም መመሪያ መስፈርት መሰረት ለመወዳደር ብቁ የሆኑ፣
ለጨረታው ከሚያቀርቡት ጠቅላላ የመጫረቻ ዋጋ 2% ( ሁለት በመቶ) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ የሚችሉ፣
አሸናፊ ተጫራቶች ውል ሲፈፅሙ ከውሉ ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ለውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ቅጂ (ኮፒ) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ዕለት ድረስ ዘወትር በሥራ ቀናት ከ2:30 እስከ 10:30 ባለው ጊዜ ውስጥ በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ ለዚህ ጨረታ በአማርኛ የተዘጋጀውን ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በመከፈል ገዝተው መወዳደር ይችላሉ።

የጨረታ ሳጥን የሚዘጋጀው በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ፊት ለፊት ባለው ኮሪደር ውስጥ ሲሆን የሰነድ ማስገቢያ ጊዜም የጨረታ ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ዕለት ድረስ ሊሆን የመከፈቻው ቀንና ሰዓት፡ሎት 01 እና02 ሚያዝያ 30 ቀን 2012 ዓ. ም. ከቀኑ በ8 ፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 8 ፡30 ይከፈታል፡፡

የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ዘግይቶ የሚደርስ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-አ/አበባ- ጃን ሜዳ ያቀድሞ ማዕከላዊ ዕዝ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ።

ስልክ ቁጥር 011-1-26 01 32/011123 42 64

በሀገር መከላከያ ሚ/ ር የመሀንዲስ ዋና መምሪያ



posted date:ዲስዘመን ሚያዝያ 16፥2012
Deadline: May 8, 2020

back

Report Page