used1

used1


በጉምሩክ ኮሚሽን አ. አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ ጽ/ ቤት የተያዙና የተወረሱ የልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 20/2012

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ

ተሽከርካሪዎችን፣ የአርማታ ፌሮ ብረቶችን
የተለያዩ የሞባይል የስልክ ቀፎዎች እና
ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡
በመሆኑም፡

በቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን በጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማሰረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ በጨረታው ዕለት ይዞ መምጣት ይኖርበታል፡፡
የሚሸጠው ዕቃ ተሽከርካሪ ከሆነ ማንኛውም ዕድሜው ከ8 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በተቁ የተገለፀ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል፡፡
ተጫራቾች የግልፅ ጨረታውንሠነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ/ በመከፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሃራጅ ጨረታውን ደግሞ በነጻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በሚወዳደሩበት ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት /ስኬጁል/ መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡

6. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- ኢአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡

7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፈሉት ዋጋ ብር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት ከተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡

9.ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

10. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥሮች ፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ 0118885511 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአ. አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ ጽ/ ቤት


Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 20፥2012

Deadline: May 7, 2020


©walia tender

Report Page