used wondo trade & investment plc.

used wondo trade & investment plc.

Walia Tender
[sponsored]

ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሚ የወጣ ያገለገለ የሰሊጥ ማበጠሪያ ማሽን ለመሽጥ የወጣ ብሔራዊ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሳሪስ በተለምዶ (ሐኪም ማሞ) የባህል ህክምና መውረጃ ላይ 100 ሜትር ወረድ ብሎ ሙሴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የቡና ማደራጃ ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ያገለገለ የሰሊጥ ማበጠሪያ ማሽን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሊገዙ ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ እና የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ ኮፒ ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያስረዳ የጨረታ ሠነድ እና በጨረታ ወቅት የሚሰጡትን ዋጋ የሚጠቅሱበት ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ) በመክፈል ይህ በድጋሚ ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት በአዲስ አበባ ዋናው መስሪያ ቤት በሚገኝበት እስጢፋኖስ ፊት ለፊት የኢት/ንግድ ባንክ መስቀል አደባባይ ቅርንጫፍ ያለበት ህንፃ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተየግ/ ማህበር 7ኛ ፎቅ ፋይናንስና ግዥ ንብረት አስተዳደር መምሪያ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሠነድ (CPO) ብር 50,000.00 ( ሃምሣ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ / ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
የጨረታው አሸናፊ የሚያስይዘው (CPO) እንደ ጨረታ ማስከበሪያ ተቆጥሮ የአሸነፈበትን ንብረት እስከሚያነሳ ድረስ ለመልካም አፈፃፀም ሲባል የሚያዝ ይሆናል፡፡
በግልፅ ጨረታው ላይ ተሳታፊ የሚሆኑት በተቁ 1 እና 2 ላይ የተገለፁትን ያሟሉ፣ የጨረታ ሰነዶችን የገዙና የጨረታውን ማስከበሪያ (CPO) ያስያዙት ብቻ ናቸው፡፡
የጨረታ ሣጥኑ የሚከፈተው በአዲስ አበባ ዋናው መስሪያ ቤት ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሚ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው አ/አ ዋናው መ/ቤት ፋይ/ግዥ/ንብ/አስ/መምሪያ 7ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
ተጫራቾች የሰሊጥ ማበጠሪያ ማሽኑን ለመግዛት በሚያቀርበው ዋጋ መግለጫ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ማህተም፣ የድርጅቱ ኃላፊ ስም፣ የድርጅቱ አድራሻና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሚ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16 ኛው ቀን የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ጠዋት 4 ፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4 ፡ 30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚደርሱ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
የጨረታው ሣጥን በሚከፈትበት ወቅት ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
የጨረታ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈውን ንብረት ማንሳት የሚችለው ሊገዛ ላሸነፈው ንብረት ያቀረበውን ጠቅላላ ዋጋ ለኩባንያው አጠናቆ ከከፈለ በኋላ ነው፡፡
ማሽኑን ለማጓጓዝ የትራንስፖርት፣ የጫኝና የአውራጅ እና ልዩ ልዩ ወጪዎችን አሸናፊው በራሱ ወጪ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ 011-5-52 10 09/011-8-69 39 79/ 011-4-42 60 33 ይደውሉ፡፡

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/ የተ/ የግ/ ማህበር



Posted: አዲስ ዘመንግንቦት 26 ቀን 2012

Deadline: June 24, 2020


© walia tender

Report Page