used kirkos manuf coll1

used kirkos manuf coll1

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ


የጨረታ ቁጥር KMC/S 001/2012 ዓ . ም


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የግንባታ ስራ ለማከናወን በቁፋሮ የወጣ ያልተፈለጠ የአርማታ ድንጋይ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መምሪያዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታ መስፈርቶች፡-

ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቶች በዘርፉ ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫት/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ እናም አግባብነት ያላቸው ህጋዊ ሰነዶች ያለው።
ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ከተደራጁበት ክ/ከተማ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ፅ/ቤት መሳተፍ እንዲችሉ የሚገልፅ ማስረጃ ከተደራጁበት የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ለጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቶች ንብረቱ፡ የሚገኝበትን ቦታ ከኮሌጁ ፊት ለፊት ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ አካባቢ በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
አሸናፊ ተጫራች ንብረቱን በሚረከቡበት ወቅት ማንኛውንም ንብረቱ ከሚገኝበት ቦታ ጀምሮ ያሉ የማስጫኛ እና የማጓጓዣክፍያዎችን ራሱ የሚሽፍን ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚያስረክቡበት ጊዜ የጨረታ ማስከበሪያ 2,000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
አሸናፊ ተጫራቶች ያሸነፉበትን ድምር ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ / CPO/ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከተቋሙ ጋር ህጋዊ ውል ይፈራረማሉ።
ተጫራቶች መረጃዎቻቸውን ዋናውንና የማይመለስ ኮፒውን በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁ. 05 ቀርበው የማይመለስ 50.00 ብር ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ እያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ ኦርጅናልና ኮፒውን የጨረታ መመሪያው በሚያዘው መሰረት ቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ፋይናንስ ቢሮ ቁ 05 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ጋዜጣው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር እስከ ከኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝና ፍሉድ ተቀባይነት የለውም ::
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣበት 11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ 4 ፡30 ሰዓት በቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ የመምህራን ማረፊያ ቢሮ ቁጥር 4 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ::
ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ፡- አድራሻ ፡- ከቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ቄራ በሚወስደው አዲሱ መንገድ ከቴሌ 200 ሜትር ወረድ ብሎ አርባ ምንጭ አሳ ቤት አካባቢ የቀድሞ ስሙ ዕውቀት አምባ ከፍ/ደ/ቴ/ት/ስ/ተቋም ግቢ፡፡
ስልክ ቁጥር 011-4-70-52-49 ወይም 011-4168823


ቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 29 ቀን 2012

Deadline: June 16, 2020


© walia tender

Report Page