used car rev232 hawassa5

used car rev232 hawassa5

ADMIN 1 TADELE

የጨረታ ማስታወቂያ

ቀጥር 21/2012


በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ ጽ/ ቤት የተተውና የተወረሰ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ፡-

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ ያገለግሉ ላንድ ክሩዘር እና ሚኒባስ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋሉ፡፡

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

ተሽከርካሪ ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ መወዳደሪ ይችላል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ-6:00 ሰዓት ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ ብር/ በመከፈል በቅ/ ጽ/ ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን (CPO) የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ፡ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ የሐራጅ ጨረታ ተሳታፊ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 ( ሃምሳ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን (CPO) ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 7 ኛተው ( ሰባተኛው) ቀን ድረስ ንብረቶችን በሀዋሳ- ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ8 ኛው ( ስምንተኛው) ቀን የግልፅ ጨረታ ጠዋት 4 ፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4 ፡15 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን የሐራጅ ጨረታው በዕለቱ፡ በ4:45 ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ይጀመ ራል፡፡ ነገር ግን ጨረታው በበዓል እሁድ/ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጥለው የስራ ቀናት ይሆናል:
ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነቫት እና ያለባት በሚል በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ ቤቱ ለመቀበል አይገደድም፡፡
ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻልአይችልም::
ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ፡ የጨረታውን ውጤት እስከ ሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል ፡፡
ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡

በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CP0 በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡

ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ባለስልጣኑ ተጠያቂ አይሆንም።
ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው፡፡

አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸ ነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎቹን ማንሳት ይኖር ባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ ጨታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቀጥር፡- 0462125396

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ / ጽ / ቤት



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 27 ቀን 2012

Deadline: June 11, 2020


© walia tender

Report Page