tx1
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የራስ ቴአትር
- የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣
- የፅዳት እቃዎች፣
- የፅህፈት መሣሪያዎች፣
- ቋሚ እቃዎች፣
- የዘመናዊ ሙዚቃ አልባሳት፣
- የባህል ሙዚቃ አልባሳት፣
- የባህል የሙዚቃ መሳሪያ እና
- የሙዚቃ ሞንታርቦ ጥገናዎች ሥራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከኢኮኖሚና ልማት ሚኒስቴር የተሰጣቸውን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 ( ሃምሣ ብር ) በመክፈል ይህን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከቴአትር ቤቱ ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዋናውና ቫት 15% በመለየት የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በቴአትር ቤቱ ይዞ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ 11 ኛው ቀን በ 4 ፡ 00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተገለፀው ቢሮ ከጠዋቱ 4 ፡ 30 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል የመክፈቻው ቀን በአልና የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የጨረታ ማስረከቢያ በየእለቱ በሚቀርበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ራስ ቴአትር ሥም ማስያዝ አለባቸው
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተያያዘው (Specification) መሰረት ገቢማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸው እቃዎች በሙሉ በራሳቸው ትራንስፖርት መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ራስ ቴአትር ሥም 10% ሲፒ በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
- አድራሻችን አራት ኪሎ እሪ በከንቱ ድልድይ በርጌስ ክሊኒክ አጠገብ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0912 00 41 04- እና 0949 83 14 97 በመደወል መረዳት ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በባህልና ቱሪዝም ቢሮ የራስ ቴአትር
___________________________________________________________________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Film/ Music and Entertainment, Installation and Maintenance, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Stationery Supplies, Purchase., Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing
Posted Date :አዲስ ዘመን ሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2012
Deadline : 2020-04-09