tx 8
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
የጨረታ ማስታወቂያ የሠራተኞች የደንብ ልብስ
ግዥ ጨረታ ቁጥር ወ. መ. ኢ. ሚ / ግፋንአ /2012/01
የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለሠራተኞች የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የዘመኑን የታደሰ በዘርፉ አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስና ፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የሠራተኞች የደንብ ልብስ ጥራቱን የጠበቀ የዕቃ ዓይነትና ጥራት ከሰነዱ ጋር አብሮ የተያያዘውን መግለጫ በሚገባ ማንበብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የተዘጋጁትን የጨረታ ሰነዶች ማንኛውም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የማይመለስ ብር 50 ( ሃምሳ ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ብር 5,000 ( አምስት ሺህ ) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ / ሲፒኦ / በማሰራት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የዋጋ ማቅረቢያ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት እስከ 5/8/2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 305 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው 5/8/2012 ዓ . ም ከቀኑ 8 ፡ 00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8 ፡ 30 ሰዓት ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መ/ ቤቱ ለአፈፃፀም የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ለመረጡት ወይም ለሁሉም እቃ መጫረት ይችላሉ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0116625524 ወይም 0116 51-11- 39 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ሀይሌ ገ/ ስላሴ ጎዳና ካፒታል ሆቴል አጠገብ
የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር
___________________________________________________________________________________
Category : Purchase., Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing
Posted Date : አዲስ ዘመን ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2012
Deadline : 2020-04-13