tex wolaita12

tex wolaita12

ADMIN 3 SELAMAWIT

የጨረታ ማስታወቂያ

በወላይታ ዞን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2012 ዓ.ም ለወረዳችን ሚሊሽያ ጽ/ቤት በመደበኛ ፕሮግም ከተያዘው በጀት ለሚሊሻ አባላት የመከላከያ ሬንጀር ደንብ ልብስ፣ ቀበቶ፣ መለዮ እና ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች፡

በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ያጠናቀቀ፡፡
የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
VAT (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
TIN(ቲን)የመለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል፡፡
በዋጋ ማቅረብያ ላይ ማህተም፤ ፊርማ፣ ቀንና ዓ/ም በግልጽ መጻፍ አለበት፡፡

በዘርፉ ዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
ተጫራቾች የተወዳደሩበት ዕቃ ናሙና በዕለቱ ይዞ የቀረቡት ብቻ ይወዳደራሉ፡፡

አሸናፊ በሆኑበት ዕቃ አቅርቦት በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ስምምነት ውል ለመግባት ፍቃደኛ ካለሆኑ ያስያዙት ሲፒኦ ብር ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 10,000.00/ አሥር ሺህ / ብር በባንክ በተመሰከረ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታው ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 50/ ሃምሳ ብር / በመክፈል ከሶዶ ዙ/ወ/ገቢዎች ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

የጨረታ ሣጥን ጋዜጣው ከወጣበት 15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 4 ፡ 30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡
ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-180-6026 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡

የወላይታ ዞን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ ኢኮ/ ል/ ጽ/ ቤት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 26 ቀን 2012

Deadline: June 17, 2020


© walia tender


Report Page