sl md የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒያም ሕክምና ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር StP/NCB/PG/003/01/2013
ኮሌጃችን ለኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት
- የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት መቅረብ የሚችል
- የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት:
- ተጫራቾች በመንግሥት ግዥ ጨረታ መሳተፍ የሚችሉት በቅድሚያ በአቅራቢነት በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በኮሌጁ የግዥ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 97 የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከሰዓት በኋላ እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የመጫረቻ ሰነዳቸውን በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የጨረታ ሳጥኑም በ15ኛ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡15 (ስምንት ሰዓት ከሩብ) ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 40,000 ብር (አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በካሽ ማስያዝ አለባቸው ::
- ኮሌጁ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112763531 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒያም ሕክምና ኮሌጅ
__________________
Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 9፣2013
Deadline:በ15ኛ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00
__________________
© walia tender