secu 8
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 03/2012
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎ/ዞን የደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2010 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጡ ሴፍ ጋርድ በረኪና 5% በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ነምበር ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የግዥው መጠኑ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /vat/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 30 ብር የኢትዮጵያ ብር ለሚወዳደሩበት ጨረታ ሰነድ በመግዛት ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 85 መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የተጠየቁትን ዕቃዎች በተሰጠው ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሙላት ያለባቸው ሲሆን፤ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው የተለያዩ እቃዎች ሆስፒታሉ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት የሚቀርብ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ዕቃ / አገልግሎት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 02% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሆኖ የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በመፈረም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ 16 ኛው ቀን እስከ ጠዋት 3 ፡ 30 ሰዓት ድረስ በሆስፒታሉ ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 85 በሚገኘው ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው 3 ፡ 30 ሰዓት ታሽጎ 4 ፡ 00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን ይከፍታል። የጨረታው ሰነድ መግዛት የሚቻለው እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሎት የሚያወዳድር ሲሆን በአንድ ምድብ ውስጥ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ውስጥ ሳይሞሉ መተው አይቻልም፡፡ በሎት ያልሞላ ተጫራችከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ደጀን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸላቸው ከ5 ስራ ቀናት በኋላ ባሉት5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ቀርበው ውል መያዝ አለባቸው፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 85 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 090456011/0587761318/ መደወል ይቻላል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ ጎ/ ዞን አስተዳደር
የደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
___________________________________________________________________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Purchase., Security and Protection, Guarding
Posted Date : አዲስ ዘመን ሐሙስ መጋቢት 3 ቀን 2012
Deadline : 2020-03-27