secu 6
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2012 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ በእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞች የደህንነት መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡
- በሥራመስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 ( ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት ።
- የጨረታ ሰነዱ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ተከታታይ ቀናት ብር 25.00 ( ሃያ አምስት) ብር / በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት ሥራ ሰዓት በመጠቀም ጨረታውን በፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ15 ተኛው / አስራ አምስተኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዕቃ ናሙናውን ይዞ መቅረብ አለበት፤
- በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል 2% በላይ ሆነ በታች ከሆነ ቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
- ዋጋውን በተሸጠው ሰነድ ተሞልቶ መቅረብ አለበት ፤
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ ኢኮ/ ልማት መምሪያ ሀዋሳ
___________________________________________________________________________________
Category : Purchase., Security and Protection, Security and Protection Equipment
Posted Date : አዲስ ዘመን እሁድ መጋቢት 6 ቀን 2012
Deadline : 2020-03-29