secu 5
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክፍለ ከተማ የደጃ/ በላይ ዘለቀ ቁ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2012 ዓ ም ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ
- ፕሪንተሮች፤
- ላፕቶፖች የቢሮ እቃዎች የማናጀር ወንበር፤
- ገስት ቸር፤
- ኮንፍረንስ ቴብል፤
- የፋይል ማስቀመጫ ሼልፍ
- የድምጽ መቅረጫዎች
- የላብራቶሪ ዕቃዎችና ኬሚካሎች (የፈዚክስ ፤ የባይሎጂ እና የኬሚስትሪ )
- የጥበቃና የጽዳት
- የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በተጨማሪም የመምህራንንና የአገልግሎት ሰራተኞችን የደንብ ልብስ ለማሰፋት የስፌት አገልግሎት ስለሚፈልግ በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት እና ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
- ማንኛውም ተጫራች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑ ግብር የከፈለና የታደሰ የንግድ ፍቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 / ሃምሳ ብር/ በመክፈል ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 04 መግዛት ይቻላል ::
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋ ጋ 2% በት/ቤቱ ስም ሲፒኦ በማስያዝ ከመወዳደሪያ ሰነዶች ጋር በቢሮ ቁጥር 04 በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘውን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናሉንና ኮፒ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታ መዝጊያው ቀንና ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 11 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትም/ ቤቱ በቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- አድራሻ፡- ከናዝሬት ት/ቤት ከፍ ብሎ
- ስልክ ቁጥር 011 156 52 46/011 126 81 22
የደጃ በላይ ዘለቀ ቁጥር 1 ሁለተኛ
ደረጃ ት/ ቤት
___________________________________________________________________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Film/ Music and Entertainment, Furnitures, Other Furniture, Laboratory and Chemicals, Chemicals and Reagents, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Photography and Filming., Photography and Filming Equipment/Accessories, Purchase., Security and Protection, Security and Protection Equipment, Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing
Posted Date : አዲስ ዘመን እሁድ መጋቢት 6 ቀን 2012
Deadline : 2020-03-27