secu 2
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የፊንፊኔ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
- የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎችን
- የፅዳት ዕቃዎችን፣
- ጎማዎችን፣
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን ፤
- የሥራ ላይ አደጋ መከላከያ እና Hesian close (ለችግኝ ጣቢያ ጥላ የሚሆን ጆኒያ) በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡
በዚህ መሠረት
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ በተጨማሪ እንዲያቀርብ ሲጠየቅ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ለሰነዱ መግዣና የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር ) ብቻ በመክፈል ዝርዝር ሰነዱን ከፊንፊኔ ቅ/ፅ/ቤት ፋ/ግ/ንብረት አስተዳደር ቢሮ ሂሳብ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ
- ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በዋጋ ማቅረቢያው ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጂናሉን ማህተምና የተጫራቾቹን ስም በማስፈር ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው ሳጥን በ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡ 00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4 ፡ 30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከስራ ቀን ውጭ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ::
- ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ገንዘብ የተጫረተበትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 5% ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የፊንፊኔ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ማስያዝ ይኖርበታል ፡፡
- ድርጅቱ ከጠቅላላ ግዢ 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለው፡፡
ማሳሰቢያ፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የጨረታ ሳጥኑ በሚከፈትበት ወቅት የተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታ ሳጥኑን ከመክፈት ድርጅቱን አያግደውም ::
አድራሻ ላም በረት የቀድሞ ዛላ ሆቴል ፊት ለፊት
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር + 251-16-464-437 በመደወል ማረጋገጥ ይቻላል ::
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
የፊንፊኔ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት
___________________________________________________________________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Stationery Supplies, Security and Protection, Security and Protection Equipment, Vehicle and Spare Parts, Tyre and Battery
Posted Date : አዲስ ዘመን ሐሙስ መጋቢት 10 ቀን 2012
Deadline : 2020-04-03