sale vi bu tex anrs n gonder1

sale vi bu tex anrs n gonder1

ADMIN 1 TADELE

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጎንደር አካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት አላቂ እቃዎች እናቋሚ ዕቃዎች ማለትም

ፕሪንተር ፣
ዲጂታል ካሜራ ፣
የፅሕፈት መሣሪያ ፣
ሕንፃና ብረታ ብረት መሣሪያዎች ፣
የብስክሌት መለዋወጫዎች ዕቃ፣
የሱፍ ክር ፣
የመኪና ክርና አክሰሰሪዎች/
የልብስ ስፌት መኪና ጥገና የዊልቸር መለዋወጫ እቃ እና
የመኪና ባትሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው፡፡

በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድና ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያቁጥር ቲን no ያላቸው፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዋጋውን 1 ፐርሰንት በዋስትና ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ማዘዣ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ሲሆን፤ የመክፈቻ ቀኑም በመጨረሻ በ15 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ጨረታው ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በማዕከሉ ግዥና ፋይ/ን/አስ/ደ/ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡
የመጨረሻው ቀን ቅዳሜ ወይም እሑድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በማዕከሉ በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡- 058 211 7233 ወይም 0918305587 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻችን ጎንደር ቀበሌ 06 እድገት ፈለግ /አሸዋ ሜዳ/ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት፡፡

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በሰሜን ጎንደር የአካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 23 ቀን 2012

Deadline: June 14, 2020



Report Page