sale kolfe k fin16

sale kolfe k fin16

Walia Tender ADMIN1
በሳምንት ውስጥ ከሁሉም ጋዜጦች ፣ድህረገጾች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት በየእለቱ የሚያወጧቸውን የጨረታ ማስታወቂያ በቴሌግራም በዚህ መልኩ ይከታተሉ ዋልያ ቴንደር ለበለጠ መረጃ 0919415260 / 0942125616 ይድውሉልን

የጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች ግዥ ለ2012 በጀት ዓመት አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ
ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ እና ምንጣፍ

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋባዛሉ:: በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ፡፡

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን በመገኘት የማይመለስ ብር 50.00( ሃምሳ ብር ብቻ) በ መክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ::

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ለሚጫረቱበት የጨረታ ሎት ዓይነት ለእያንዳንዱ ብር የዋጋውን (1% አንድ ፐርሰንት ) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን (ኦርጅናል) እና አንድ ፎቶ ኮፒ ለየብቻው የድርጅቱን ስም፣ አድራሻ በመጥቀስ እና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ለዚህ ስራ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ6፡30 ሰዓት ድረስ አስመዝግበው ማስገባት አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡበት (የሚሰሩበት) የነጠላ ዋጋ በሰነዱ ላይ በመግለጽ ሙሉ አድራሻና ማህተም መጠቀም አለባቸው፡፡

የጨረታ ሰነዱ ማቅረቢያ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 2 ፡30-6 ፡30 ሰዓት ተመልሶ በዕለቱ ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር በድን ቢሮ ይከፈታል፡፡

የግዥ ውል በሚፈጸምበት ጊዜ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰው ሎቶች ግዥ ብዛት የገባው ዋጋ ሳይቀየር አስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስም የሚችል መሆኑን ተጫራቾች አውቀው መጫረት ይኖርባቸዋል ፡፡
ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

***ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ***

አድራሻ፦ ቤተል ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ስመገብ ያስው ህንጻ ሳይ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍስ ከተማ አስተዳደር ያዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605-04

ስልክ ቁጥር 0118330765

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 26 ቀን 2012

Deadline: June 13, 2020


© walia tender

Report Page