sale bui arbaminch teaching1

sale bui arbaminch teaching1

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ2012 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዥዎችን ማለትም

የጽዳት ዕቃዎችን
የጽህፈት መሳሪያዎችን
የኤሌክትሪክ ና የቧንቧ መስመር መለዋወጫ ዕቃዎችን

በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ስመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

ከስራው ጋር የተገናኘ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ
በመንግስት ግዥ ለመሣተፍ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (Tin No) ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ተጫራቾች የጨረታ መመሪያና የዕቃ ዝርዝር መግለጫ የሆነውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ ሰነዱን በማይመለስ ብር 100 በመግዛት የአንዱን ዕቃ ዋጋ ከነቫቱ በመሙላት የፋይናንሻል ዶክመንት ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡

በተራ ቁጥር 1 እና 2 ለተጠቀሱት ዕቃዎች ናሙና የሚቀርብ ሲሆን አስቀድመው ለተመረጡ ናሙናዎች ብቻ ዋጋቸው የሚነበብ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ብር 20,000.00 በጥሬ ገንዘብ ወይም በአካባቢው በሚገኝ ባንክ ወይም በእነሱ ቅርንጫፎች CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተራ ቁጥር 1 ለተጠቀሰው ዕቃ በ 16 ኛ ቀን ከረፋዱ 3 ፡ 30 ተዘግቶ 4 ፡ 00 ሰዓት፤ በተራ ቁጥር 2 ለተጠቀሰው ዕቃ በ17 ኛ ቀን ከረፋዱ 3 ፡30 ተዘግቶ 4:00 ፤ ሰዓት እንዲሁም በተራ ቁጥር 3 ለተጠቀሰው ዕቃ በ18 ኛ ቀን ከረፋዱ 3 ፡30 ተዘግቶ 4:00 ፤ በኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0468812071/0912083885 ደውለው ይጠይቁ፡፡

አርባምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 26 ቀን 2012

Deadline: June 18, 2020


© walia tender

Report Page