sale SSNP AN1

sale SSNP AN1

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 113/12

የሀገሪቱ / የክልሉ ስም:- የደቡብ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መንግሥት

የቢሮ ስም፡- እንስሳት እና ዓሣ ሀብት ቢሮ

የፕሮጀክት ስም፡- የእንስሳትና ዓሣ ሴክተር ልማት ፕሮጀክት

የፕሮጀክት መለያ ቁጥር፡ P159382

የብድር ቁጥር : IDA 6650

የጨረታ ማስታወቂያ ስም፡- ለአርሶ አደር ማሰልጠኛ ጣቢያዎች የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ግዥ

የውል/ የጨረታ ቁጥር፡- ET-SR LESDP-171560-GO-RFB

የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ቢሮ የእንስሳትና ዓሣ ሴክተር ልማት ፕሮጀክት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተመለከቱትን ለአርሶ አደር ማሰልጠኛ ጣቢያዎች የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ከዓለም ባንክ በተገኘ በጀት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

page1
page 2
page3

በመሆኑም በንግድ ዘርፉ የአቅራቢነት ፈቃድ ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የVATተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ የሚያቀርቡተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች በዘርፉ ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸውን የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ለመጫረት የሚቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ / ባንክ ጋራንቲ/ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ኛው ቀን 9 ፡ 00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል ከቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ  የቴክኒካልና የፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግና ሲፒኦ /ባንክ ጋራንቲ/ በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ በመክተትና አጠቃላዩን በአንድ ፖስታ በማሸግ በቢሮ የግዥ ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

የጨረታ ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 30 ኛው ቀን ከቀኑ 9 ፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9 ፡ 15 ሰዓት ተጫራቾች/ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ግዥ ኬዝ ቲም ክፍል ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 30 ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመክፈቱ ሥነ - ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡
ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ እልፍ እንዳሉ ወደ ሥላሴ መሄጃ መንገድ ላይ ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: 046 212 17 16/046 212 61 01/046 212 61 11

በደቡብ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መንግሥት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ቢሮ

/ ሀዋሳ/


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 25 ቀን 2012

Deadline: July 2, 2020


© walia tender

Report Page