sale 521 sheger13

sale 521 sheger13


ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SMTSE/ ግጨ/18/2012/2020

ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ግብዓቶችን

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና
ሌሎች የቪዲዮ ካሜራ መለዋወጫ አቅርቦት በሃገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ ደብዳቤ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን (Tax Clearance)፣በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (VAT Registration) የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት(TIN Certifcate) ማቅረብ አለበት፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር) በመያዝ 22 እየሩስ ህንጻ፣ 7ኛ ፎቅ፣ ሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የግዥና ንብ/አስተ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7-07 መውሰድ የሚችሉ ሆኖ የጨረታው ሰነድም በዚሁ አድራሻ በመምጣት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት አንድ ብ ር 5,000.00 ( አምስት ሺህ ብር) በሲፒኦ አ ልያም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
የጨረታ ማስከበሪያው ከህጋዊነት ማረጋገጫ /ከቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል ጋር መቅረብ አለበት፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከወሰዳችሁበት ቀን ጀምሮ በተራ ቁጥር 2 በተገለፀው አድራሻ እስከ ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ. ም ከ8 ፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታው ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ። የእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ ከላይ በተገለጸው ቀንና ቦታ ሆኖ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8 ፡00 ተዘግቶ ከቀኑ 8 ፡30 የሚከፈ ት ሲሆን ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዳቸው ሎቶች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ዶከመንት ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ፣በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
የሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር፡ 011-8-33-34-62 /0118-33-40-76/ ጨረታው ን የሚመለከቱ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 18 ቀን 2012
Deadline: June 5, 2020


© walia tender

Report Page