sale 42

sale 42


የጨረታ ቁጥር አመሥድ 03/2012

ክፍል አንድ

አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት

የMC-3000 ቢትመን ሽያጭ ግልጽ ጨረታ

ድርጅታችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፀውን የMC-3000 ቢትመን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ተወዳዳሪ ድርጅት ወይም ግለሰብ በድርጅታችን ዋናው መ/ቤት ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡

ተጫራቾች በድርጅታችን ስም ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲ. ፒ. ኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
መ/ቤቱ አሽናፊውን ተጫራች ድርጅት ወይም ግለሰብ በሚመርጥበት ጊዜ የሚሸጠውን ቢትመን መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 50% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ ለተገለፁት እቃዎች የሚያቀርቡበትን መግዣ ዋጋ በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሰውን ቢትመን በድርጅታችን ፍቼ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት በአካል መጥቶ ማየት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም ፋይናንሽያል ሰነድ አዘጋጅተው እስከ 20ኛው ቀን ድረስ ባህርዳር ከተማ በሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው በ 20 ኛው ቀን ከቀኑ 9:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9:30 ይከፈታል፡፡
በጨረታው ለተገለፁት እቃዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ብር 100.00 ( መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከድርጅታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡ በዚህ ቀን ውስጥ ውል ካልወሰደ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡
በተጨማሪም አሸናፊው ድርጅት ውል ከወሰደ በኋላ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እቃዎችን ሙሉ በሙሉ ማንሳት አለበት፡፡ በተባለው ቀን ካላነሳ መ/ቤቱ ለሌላ ድርጅት የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን አሽናፊው ድርጅት እቃዎችን መርጦ መውሰድ ወይም መተው አይችልም፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 35-76 መደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት



_______________________________
Category : Construction and Construction Machinery, Construction Raw Materials, Sale.

Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 25 ፥2012
Deadline :2020-04-22

Report Page