rev87 used mojo12

rev87 used mojo12


በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ
ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ / ቤት
የተተው ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ቁጥር ግ 19/2012 ጨረታ
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎችን በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 51፣ ንዑስ አንቀፅ 1 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ከ1160/2011 አንቀዕ 13 ንዑስ አንቀፅ መሰረት ዕቃቸውን የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ፈጽመው ባለመወሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው ተቆጥረዋል፡፡ ስለሆነም በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ያሉ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በአወጣው መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም የህንፃ መሣሪያዎች፣ ምግብ ነክ፣ የህትመት መሣሪያዎች፣ ማሽኖች፤ የፋብሪካ ግብዓቶች፣ ፕላስቲክ ባግ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ከሮች እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ ሙግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ) በመከፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቶች በጨረታ ከሚሽጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500 ሺህ በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የ15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ::
ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበ ሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታው ከመከፈቱ፡ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው እንደታወቀ በ3 (ሶስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከአሸነፈበት ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ይሆናል:: ተጫራቾች የሚያስይዙት cPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስም ( ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODO BRANCH OFFICE) ስሚል ሲሆነ የግል ባንክ ከሆነ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ቅርጫፎች፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሆነ ደግሞ ከአዲስ አበባ ፣አዳማና ሞጆ ቅርጫፎች መዘጋጀት አለበት::
የግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ፣ የሞሉበት ሠነድ፣ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሽግ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት ጠዋት 3፡45 ሰዓት ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል።
የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀን ጨምሮ በ8 ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3:45 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቱ ለጨረታ ሰአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም::
ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ጨረታውን ለማሸነፍ ሲል መደለያ የሰጠ ወይም ለመስጠት የሞከረ ማንኛም ተጫራች ከጨረታው ይወገዳል፡፡ ጨረታው ከተካሄደ በኋላም ቢሆን ጨረታ አሸናፊው ጨረታውን ያሸነፈው በህገ-ወጥ መንገድ መሆኑ ከተረጋገጠ የጨረታው ውጤት ይሰረዛል ፡፡
ማንኛውም የጨረታ ሽያየዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡
ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፡፡
ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
የግልጽ ጨረታው አሸናፊው ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉብትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡ ያሸነፉት ዕቃም በድጋሚ ለጨረታ ሽያጭ ይቀርባል፡፡
በተራ ቁጥር 12 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ (ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል፡፡
እሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሽጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-0222360190 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ

ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ

ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 15 ቀን 2012

Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page