rev Used kality217

rev Used kality217


የጨረታ ማስታወቂያ


በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ያገለገሉ የቤትና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታና ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ለመወዳደር የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል

በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 6 ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ሳሪስ አቦ ኖክ የነዳጅ ማደያ አጠገብ ከሚገኘው አዲስ ህንፃ አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 507 በመቅረብ የዕቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ብር 50 ( ሃምሳ ብር) በ መግዛትና በኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት (የቀድሞ ኮሜት ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር) ግቢ በአካል በመቅረብ ዕቃዎችን መመልከት ይችላል::

ተጫራቾች ለተወዳደሩባቸው ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 20% ሲፒኦ በማሠራት ከጨረታው ሠነድ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል :: ተጫራቶች ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊ ከሆኑ ተደምሮ የሚከፈል ሲሆን፣ በጨረታው ከተሸነፉ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

ዋጋ ለመስበርና በተለያየ መንገድ ፍትሐዊ ውድድር እንዳይኖር በነጠላ ወይም በቡድን በሚመሳጠሩት ላይ ቅ/ጽ/ቤቱ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ፡፡

በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቶች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መከፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጐ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

አሸናፊ ተጫራቶች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃልለው በመከፈል ዕቃዎችን 10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው::

ጨረታው ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 3 ፡30 ሰዓት በቅ/ ጽ/ ቤቱ ቢሮ 8 ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

***ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 0114403746 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ:: ****

የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ ጽ/ ቤት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 22 ቀን 2012

Deadline: July 18, 2020


© walia tender

Report Page