rent har 12

rent har 12


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር EPSA/SERV.05/2012

የመጋዘን ኪራይ ጨረታ

የኢፌዴሪ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ወደ ሀገር ውስጥ ገዝቶ ለሚያስገባቸው የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ ዕቃዎችን በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተማ ለሚያከማችበት ደረጃውን የጠበቀ መጋዘን ህጋዊ የሆኑ ድርጅቶችን አወዳድሮ የኪራይ አገልግሎት ውል ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::

የ2012 በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤ በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ እንዲሁም ሌሎች የህጋዊነት ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ።

ተጫራቾች መደበኛ የጨረታ ሰነዱን ከመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ብር 200.00 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ተመላሽ የሚሆን ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺ ብር/ ሲፒኦ /ETHIOPIAN PHARMACIUTICAL SUPPLY AGENCY/ስም አለባቸው።

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ሰኔ 12/2012 ዓም ከቀኑ በ7 ፡30 ሰዓት ብቻ ማቅረብ አለባቸው::
ጨረታው ሰኔ 12/2012 ዓ. ም ከቀኑ 7 ፡30 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8 ፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ውጭ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

ኤጀንሲው ጨረታውን በተመለከተ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡- የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር-+251 112765294

ፖ. ሳ. ቁ -21904

አዲስ አበባ

የኢፌዲሪ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 23 ቀን 2012
Deadline: June 19, 2020


© walia tender

Report Page