pr,tex,jan,comp

ለ2 ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የቂ/ክ/ከ/ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2012 ዓም በጀት አመት ለቢሮ መገልገያ የሚሆን ዕቃዎችን
ሎት 1፡- ቋሚ ዕቃዎችና ፕሪንተር ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ሎት 2፡- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
ሎት 3፡- ቋሚ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን
ሎት 4፡- የጽዳት ዕቃዎችን
ሎት 5፡- የሰራተኛ ደንብ ልብስ
ሎት 6፡- ህትመት
ሎት 7፡- ኮምፒዩተርና ፕሪንተር ጥገና
ሎት 8፡- የመስተንግዶ አገልግሉት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ ቲን ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ፈቃድና የአገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በቂርቆስ ክ/ከ/ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 መግዛት ይችላሉ፡፡
3.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ የቂ/ክ/ከ/ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 ቀርበው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ዕቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ወጪ እስከ መቱ ድረስ ማቅረብ አለበት ፡፡
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች በጨረታው ስፔስፊኬሽን መሰረት ብቻ መሆን አለበት፡፡
6. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ላይ 10 ፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10 ፡45 የሚከፈት ይሆናል፡፡
7.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅና መመሪያ መሰረት በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
9. የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት 3,000( ሶስት ሺህ ብር)
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ሲያሰራ ለቂ/ክ/ከ/ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ብሎ ማስራት ይኖርበታል፡፡
አድራሻችን፡- አጎና ሲኒማ ፊት ለፌት ከያሬድ ቤተ ክርስቲያን ከፍ ብሎ መስቀል ፍላወር አጠገብ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ ቤት ህንፃ
ለተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0114168227
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ ቤት
_______________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Electrical and Electronics, Electronics Equipment, Food and Beverage, Catering Service, Installation and Maintenance, Office Supplies and Stationery, Office Items and Equipment, Office Equipment Maintenance, Printing and Publishing., Printing and Publishing Service, Purchase., Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 15 ፥2012
Deadline :2020-04-06