print oromia commun1

print oromia commun1

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በ2012 ዓም የበጀት ዓመት ብዛት 5,000(አምስት ሺህ) መጠኑ 17.145 (W) X24.13 (H) (6.75 x9.5 ኢንች)፣ የውጭ ልባሱ 250 ግራም የአርት ወረቀት፣ የውስጥ ገጾችም በባለ 100 ግራም አርት ወረቀት ሆኖ ልባሱም ውስጡም ባለሙሉ ቀለም፣ አጠራረዙ በክር ተሰፍቶ ፐርፌክት ባይንዲንግ፣ የገጽ ብዛቱ 500 ላሚኔትድ የሆነ ዓመታዊ መጽሐፍ ማሳተም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዛችኋል፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣
ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በተጨማሪ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ከቢሮ በተሰጠው ፎርም ላይ ሞልቶ የሚያቀርቡ ሲሆን በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወሰዳል፡፡ በቁጥር በተፃፈውና በፊደል ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው ይወሰዳል፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተመሰከረለት ሲ ፒኦ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፣
በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቶች ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፣
አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሠረት ሥራውን ለመፈፀም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ10 በመቶ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ(CPO) ውሉ መፈፀሙ እስኪረጋገጥ ድረስ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
ከዚህ በላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ውሉን በአግባቡ ሳይፈፅሙ ሲቀሩ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለቢሮው ገቢ ይሆናል፣
ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸው በትክክል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው፣
ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት፣
ተጫራቾች ያቀረቡትን ዋጋ የመቆያ ጊዜ (Price Validity Date) ከጨረታው መክፈቻ ዕለት ጀምሮ የሚፀናበትን ጊዜ፡ ስራውን አጠናቀው የሚያስረከቡበትን ጊዜ (Delivery Date) መግለፅ አለባቸው፣
ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኦሮሚያ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ 9ኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀና ት የማይመለስ ብር 100/ አንድመቶ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ የሰነዱን ዋናና ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ 9ኛ ፎቅ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣ በኋላ በ16 ኛው የሥራ ቀን በ4 ፡00 ሰዓት ይዘጋል። በዚህ ዕለትም በ4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾ ች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ 9ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፡፡
ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ፊላሚንጎ በሚገኘው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መስተዳደር ጽ/ ቤት ግቢ

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0115154615

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 28 ቀን 2012

Deadline: June 20, 2020


© walia tender


Report Page