other den sidama aleta1

other den sidama aleta1


ለ3 ተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ መንግስት ሲዳማ ዞን የአ/ወ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት ከፍተኛ የደን ሽያጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች፡

በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላችሁ፣
የ2012 ዓ.ም ግብር ከፍላችሁ ፍቃዳችሁን ያሳደሳችሁ፣
የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርፍኬት ያላችሁ፣
የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላችሁ፣
አግባብነት ካለው ከመንግስት ተቋም የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆናችሁ፣
የእንጨት መቁረጫ ማሽነሪ ስለመኖሩ መረጃ ማቅረብ የሚችል እና መረጃውን ከቴክኒክ ሠነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
ተጫራቹ ካስገባው ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ከቴክኒካል ሠነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ህጋዊ ፈቃዳቸውንና (VAT) የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር / አ/ወ/ወ/ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመክፈል ከአ/ወ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስግዢ ቢሮ ቁጥር 10 የተዘጋጀውን ሠነድ መውሰድ የሚችል፡፡
ከመንግስት ግብር ነፃ ስለመሆናችሁ የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
ከዚህ ቀደም ለሠራችሁት ሥራ የመልካም ሥራ አፈፃፀም የምስጋና የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባችሁ፡፡
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታ ሠነድ ኦርጂናል ቴክኒካል ለብቻ፣ቴክኒካል ፎቶ ኮፒ ለብቻ ይታሸጋል እንዲሁም ፋይናንሻል ኦርጅናል ለብቻ ፋይናንሻል ፎቶ ኮፒ ለብቻ በማድረግ በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም ኤንቨሎፕ በማሸግ አ/ወ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚችል ሆኖ በፋይናንሻል ሠነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ዶክመንት ላይ ሕጋዊ የድርጅታችሁን ወይም የማህበራችሁን ማህተም ማሳረፍ አለባችሁ፡፡
ተጫራቾች ለሚጫረቱትን የደን ሀብት ውጤት እስከ ቦታው ድረስ አይተው ከአ/ወ/ወ/አካ/ጥ/ጽ/ቤት ስለማየትዎ የሚገልጽ ህጋዊ ማህተም ያለው ደብዳቤ በመውሰድ ከቴክኒካሉ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈውን ደኖች (ዕንጨት) በወር ጊዜ ውስጥ ቆርጦ ማንሳት አለበት፡፡ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በ 4 ፡ 30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በሰዓቱ መገኘት ሳይችሉ ጨረታውን የጨረታ ኮሚቴው መክፈት የሚችል መሆኑን እየገለጽን፣ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0462241030

የደ/ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መንግስት ሲዳማ ዞን አ ለ ታ ወንዶ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 23 ቀን 2012

Deadline: June 14, 2020


© walia tender

Report Page