other Dara1

other Dara1


የጨረታ ማስታወቂያ

የሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ ለ4ኛ ጊዜ ለ2012 በጀት አመት የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት

ይፈልጋል በዚህም መሰረት ዝርዝራቸው በሚመለከተው ሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል::

በዚህ ጨረታ መሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያስባችሁ ማስረጃ

ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ እንዲሁም በግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለሎት 1 ፣ ለሎት2 50/ ሃምሣ ብር / በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኤጀንሲው የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 413 በመቅረብ ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
ለሁሉም የአገልግሎት ግዥዎች ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትእዛዝ /CPO/የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በሚል በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በማሸግ የጨረታ ቁጥርና የእቃውን አይነት በግልጽ ፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታው ሣጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 413 ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16 ኛው የስራ ቀን በ5:00 ሰአት የጨረታው ሣጥን ተዘግቶ/ ታሸጐ/ በ16 ኛው ቀን በ5:30 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል፡፡
ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ሜክሲኮ አልሣም ጨለለቅ ህንፃ

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ 4 ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 413

ስልክ ቁጥር 011-55897-99

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ

አዲስ አበባ


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 21 ቀን 2012

Deadline: June 18, 2020


© walia tender

Report Page