media DMU

media DMU

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

ብግጨ 44/2012

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2012 የበጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበለት በጀት

ሎት1፡-የሙዚቃ ዝግጅትና
ሎት 2 የአዳራሽ ዲኮር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ስራውን መስራት የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-

1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1 ፤- ብር 10,000.00 / አስር ሺ ብር/
ሎት 2 ፤ ብር 10,000.00 / አስር ሺ ብር/

በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሠርተው ማቅረብ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሠራት ማቅረብ አለባቸው፣

3. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡

4. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ የጨረታ ዶከመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

5 ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሽግ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 በሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣

6. ጨረታው በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጨረታ ው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡

7. የጨረታውን ፋይናንሽያል ኦርጅናል ዶክመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ሊኖርባቸው ፋይናንሽያል ዶክመንቶች ከኦርጅናሉ በተጨማሪ አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡

8 ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሣሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0587716691 ደብረ ማርቆስ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 27 ቀን 2012

Deadline: June 19, 2020


© walia tender

Report Page