land 2
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ SSNT-T0193
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ (ተርሚናል 2 እና ተርሚናል 1) ፊት ለፊት የሚገኘውን የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) አገልግሎት (Car Parking service) መስጫ ቦታን በገቢ መጋራት(Revenue Sharing) መርህ መሰረት አገልግሎት መስጠት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ማንኛውም ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ስም የምስክር ሰርተፊኬት፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ VAT/TIN የምዝገባ ምስክር ሰርተፊኬት ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 / አንድ መቶ ሽህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ / ሲፒኦ/ ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር/ አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T0193 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካል ፕሮፖዛል, ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል እና ሲፒኦ) ኦርጂናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች ውስጥ በማስገባት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ. ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የሠራተኞች መመገቢያ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ. ም ከቀኑ በ 9 ፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለ ተጨማሪ ማብራሪያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-5178918
ኢ- ሜይል: BirtukanS@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙ ሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
___________________________________________________________________________________
Category : Land and Lease, Rent.
Posted Date : አዲስ ዘመን ረቡዕ መጋቢት 2 ቀን 2012
Deadline : 2020-04-08