joint opening session
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የመክፈቻ ንግግር ለ
• የለውጥ እቅስቃሴው ዘርፈ ብዙ እንዲሆን ጥረት ተደርጓል።
• በፖለቲካ ኢኮኖሚ እና ሌሎች ጉድለቶችን ለማቃናት ጥረት ተደርጓል።
• 2012 የለውጡን ጉዞ የተሻለ መሰረት የምናሲዝበት ይሆናል።
• በተለይም የጠቅላይ ሚኒስትሩን የመደመር እሳቤ መሰረት አደርጎ ይጓዛል።
• ይህም ሀገራዊ አንድነት ማስጠበቅ፣ የህዝቧን ክብር ማስጠበቅና ብልፅግናን ማምጣት ግብንም ተይዟል።
• በልዩነታችን ላይ የሰራነውን ያህል አንድ በሚያደርጉን ላይ አልሰራንም፤ የኢኮኖሚ አድገቱ ሁሉንም ተጠቃሚ አላደረገም።
•በለፉት ጊዚያት በውስጣዊ ችግሮች 2 ሚሊየን ያህል ዘጎች መፈናቀላቸው ጥቁር ጠባሳን ጥሎ አልፏል፤ ተፈናቃዮችን ለመመለስ በተሰራው ስራ አሁን ላይ ከ100 ሺህ ዎች ያማይበልጡ ተፈናቃች ብቻ መቅረታቸውን ገልጸዋል፡፡
•ወደፊትም ቀሪ ተፋናቃዮችን ቀደ ቀያቸው የመመለስ እና መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ ቀዶሞ መከላከል ፣ላይ ይሰራል፡፡
•“የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማትን እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊትን የሕጋዊ ማዕቀፎችና አቅሞችን በማዳበርና በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ አሁን በሀገራችን ያለውን አንጻራዊ ሠላም ወደ አስተማማኝ ሠላም ለማሳደግ በትኩረት ይሠራል፡፡
•በቀጣይ ሀገራችን የምታስተናግዳቸውን ሀገራዊ ምርጫ እና ሌሎች ክስተቶች ሠላማዊ በሆነ መልኩ ለመፈጸም የሚያስችል አቅም ይፈጠራል።”
•መንግስት የፖሊቲካ ምህዳሩን ለማስፍት በህግ አሰራሮች እና አደረጃጀቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል፡፡
•ወደፊት የሚካሄደው ምርጫ ነጻ ፍትሀዊ ታማኒ አሳታፊ ምዕላተ ህዝቡን ያሳተፈ እንዲሆን ይረጋል፡፡
•ለዚህም ዜጎች የመገናኛ ብዙሃን እና የሌሎች በላድርሻ ተሳትፎ ያስፈልጋል፡፡
•መንግስት ምርጫው ባለፉት ጊዚያት የታዩ ግድፈቶችን የሚታረሙበት እንሰዲሆን ይሰራል፤ ህገ ወጥ ረተግባራት ሲያገጥሙም በህግና ስርዓት የማስተካከል ስራ ይሰራል፡፡
•የፍርድ ቤቶች አራር በማሻሻልበዓመት እስከ 250 ሺህ መዛግብት ለማስተናገድ የሚያስችል አወቃቀር መፍጠር፤ የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መምሪያ፣ የቁጥጥርና ክትትል ክፍሎችን በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች ማቋቋም እና ማደራጀት፤ ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓትን ማጠናከር፤ የዳኝነት አገልግሎት ሥራ ደጋፊ የሆኑትን የአስተዳዳር አካላት ውጤታማነት ማረጋገጥ ዋነኞቹ ትኩረቶቹ ናቸው።
•በ2012 ኢኮኖሚውን ጤናማ ለማድረግ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ የኤክስፖርት ምርት ላይ፣ የስራ እድል ፈጠና ፣ የገቢ አሰባሰብ እና ኢንቨስትመንት የማሻሻከል ስራዎች ይከናዎናሉ፡፡
•ምርት እና ምራታማነትን ለመሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል፡፡
•“ኮንትሮባንድ፣ ታክስ ማጭበርበርንና ታክስ መሰወርን፣ እንዲሁም በሕቡዕ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን ወደ ሕጋዊ ሥርዓት በማምጣት ኢኮኖሚውን ወደ ተሻለ ጤንነት የማሸጋገር የተቀናጀ ሥራ ይከናወናል፡፡”
•“በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ የሥራ ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን የተጀመረው በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለወጣቶቻችን የሥራ ዕድሎችን የማመቻቸትና የማፈላለግ ተግባራት ይበልጥ ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡
•የመስኖ ግድቦች ሌሎች በያዝነው በጀት ዓመት የመግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፤ በዚህ ዘርፍ ለ12 ሺህ ያህል ወጣቶች የስራ እድል እንደሚፈጠር ነው የተናገሩት፡፡
•“ሀገራዊ የማዳበሪያ አቅርቦት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታትና በዓመት ከግማሽ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚወጣውን የውጪ ምንዛሪ ለማስቀረት አዲስ የማዳበሪያ ፋብሪካ ድሬዳዋ ላይ ለማቋቋም ከአንድ የውጭ ኩባንያ ጋር ሽርክና በመፈራረም ሥራው በቅርቡ ይጀመራል።”
•“በዚህ ረገድ የ2010/2011 ምርት ዘመን የሰብል ምርትን 406 ሚሊዮን ኩንታል ለማድረስ ታቅዶ 316 ሚሊዮን ኩንታል ማለትም 78% ለማምረት ተችሏል፤ ይህም በ2009/2010 ከተመረተው 267 ሚሊዮን ኩንታል ጋር ሲነፃፀር የ4.29 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡”
•“ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በግንባታ ላይ ያሉ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው እንዲፋጠን ይደረጋል፡፡
•በመንግሥትና በግል አጋርነት የሚሠሩት 10 ፕሮጀክቶች ሥራቸው ይጀመራል።
•የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቱን ከማስፋትና ተደራሽነትን ከማሳደግ አኳያ በአራት መቶ አምስት የገጠር ቀበሌዎች እና መንደሮች አንድ ሚሊዮን ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል።
•“በገጠር ወደ ሃምሳ ሺ የሚጠጉ አዳዲስ የውሃ ተቋማት ግንባታና ከ13 ሺህ በላይ የማይሠሩ ተቋማትን መልሶ የማቋቋም ሥራ ይከናወናል፡፡
•በከተማ ደግሞ 60 የመጠጥ ውሃ ተቋማት ጥናቶችን፣ 60 አዳዲስ ግንባታዎችንና 30 የመልሶ ማቋቋም ሥራዎችን ለማካሄድ ታቅዷል።”
•“የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሳተላይት በያዝነው ዓመት በታኅሣሥ 2012 ዓ.ም. በቻይና ከሚገኝ የማምጠቂያ ማዕከል ወደ ጠፈር ይላካል፤ ሳተላይቱ ለግብርና፣ ለደን ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ መረጃዎች ለመቀበል ይውላል።
•በቴሌኮም ዘርፍም በበጀት ዓመቱ የኤትዮ ቴሎኮም ጨምሮ ሶስት የቴሌ ኦፕሬተሮች ይኖሩናል፤ ለዚህም ሁለት ዓለም አቀፍ ቴሌኮም ኦፕሬተሮችን አወዳድሮ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ስራ ይሰራል።
•በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ወደ ተግባር የማስገባት ሥራዎች ይሠራሉ፤ የተጀመረው ረቂቅ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ እንዲሁም የትምህርት ሕግ ተጠናቆ ወደ ሥራ ይገባል።
•"ሆስፒታሎቻችንን ለሕሙማንና ለጤና ባለሞያዎች በሚመጥን መልኩ የማሻሻያ ፕሮግራሙ ‹ያገባኛል› በሚል መርሕ፤ በ24 ሆስፒታሎች የማሻሻል፣ የማዘመንና ደረጃቸውን የማሳደግ ላይ በትኩረት ይሰራል።
•“የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግና ብሎም የጾታ እኩልነት ማረጋገጥ በ2ዐ11 የተመዘገቡ ውጤቶችን በ2ዐ12 ዓ.ም ጽኑ መሠት እንዲኖራቸውና እንዲሰፉ የማድረግ ተግባር ልዩ ትኩረት የሚሻ ይሆናል፡፡”
•“በ2012 ዓ.ም የበጀት ዓመት በባሕል ዘርፍ ለእደ ጥበብ ዘርፍ የአቅም ግንባታና የገበያ ትስስር ሥራ ለመሥራት፣ ኪነ ጥበብ ለሀገር ሠላም ግንባታ የሚውልበትን አሠራር ዘርግቶ ለመተግበር ታቅዷል፡፡
•ከቅርስ ጥገናና እንክብካቤ አንፃር የላሊበላ፣ የአክሱም፣ የአባ ጅፋርና የጎንደር አብያተ መንግሥት ቅርሶች ጥገና ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ይሠራል፡፡”