harj 03

harj 03


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለ መብት አቶ ፍቃዱ ፍሬው እና ፍባለዕዳ አቶ ዘላለም ደቻሳ መካከል ስላለው የፍ/አፈፃፀም ክርክር ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 280964 በ29/05/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠውን ትዕዛዝ መሰረት በአቃቂ ቃሊቲ ጉምሩክ ኮሚሽን ቃሊቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኝ ተሽከርካሪ ማለትም 1ኛ. የሻንሲ ቁጥር MROFR22EOD0704860 የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 950,000 (ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ሺ ብር ሆኖ የስም ማዘዋወሪያ ዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 19 ቀን 2012 ዓም በሐራጅ ያሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4 ፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡ ፡ 2ኛ. በዚሁ ግቢ የሚገኝ ሌላኛው ተሽከርካሪ የሻንሲ ቁጥር MROFR22G8Do70554 የሆነ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) ሁኖ የስም ማዘዋወሪያ ግዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 19 ቀን 2012 ዓም በሐራጅያሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4 ፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የስራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱን ለማስጎብኘት በሚመቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱ ግምት 1/4 ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታው ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በተጨማሪ ተጫራቶች ታክስ ስም ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ ሐራጁ ጎድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የኢ. ፌ. ዴ. ሪ ጠቅላይ ፍ/ ቤት የፌዴራል ፍ/ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት



_______________________________
Category : Foreclosure., Vehicle Foreclosure, Sale., Vehicle and Spare Parts, Vehicle Sale

Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 18 ፥ 2012
Deadline :2020-04-27

Report Page