firn tex Dmu 3

firn tex Dmu 3

Admin1

የጨረታ ማስታወቂያ

ብግጨ 86/2012

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2012 የበጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበለት በጀት

ሎት 1 ፡- ፈርኒቸር እና
ሎት 2 ፡- የስፖርት ትጥቅ / ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ሥራውን ለመሥራት የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ ፣
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት 1 ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ / እና ለሎት 2 ብር 50,000.00/ ሃምሳ ሺህ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሠርተው ማቅረብ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሠራት ማቅረብ አለባቸው፣

አሸናፊው ተጫራች አሽናፊነቱ በተገለፀለት ከ7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ስማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፣

ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ የጨረታ

ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ / በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣
ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ በ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3 ፡ 59 ድረስ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
ጨረታው በ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡ 00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡ 30 በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታውን ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡

የጨረታውን ፋይናንሽያል ኦርጅናል ዶክመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን መሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ ኣንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ሲኖርባቸው ፋይናንሽያል ዶክመንቶች ከኦርጅናሉ በተጨማሪ አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሣሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 05877166-91 ደብረ ማርቆስ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 23 ቀን 2012

Deadline: June 15, 2020


© walia tender

Report Page