energy 2
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የቡራዩ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
- የውሃ መሳቢያ ፓንፕ ፤
- የተለያዩ መጠን ያላቸው የውሃ ቆጣሪዎችን እና
- ለቢሮ ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ ድምፅ አልባ ጀነሬተሮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾች በድርጅቱ ጽ/ቤት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
- ተጫራቶች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቲን ሠርተፍኬት ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቶች የመልካም ሥራ አፈጻጸም ከሥራው ጋር ተያያዥነት ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ጋር ኦርጅናሉንና ኮፒው ለየብቻው በታሸገ የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በመጥቀስ በትክክል በመሙላት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር፡
- i. ለውሃ መሳቢያ ፓንፕ .………300 ብር
- ii. ለውሃ ቆጣሪ .……........ 300 ብር
- iii.ለጀነሬተሮች .……….....… 200 ብር በመክፈል ከቡራዩ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ቀርበው ሰነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 10 ( አሥር ) ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ የሚውለው የሥራ ቀን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ5:00 ሰዓት ላይ በድርጅቱ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል ፡፡ 10ኛው ቀን ቀጥሎ የሚውለው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡ :
5.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 ብር / አሥር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) በማስያዝ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ በመሙላት በፖስታ ውስጥ በመጨመር ከፋይናንስ ዶክመንት ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6.በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚገኝ አካል የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
7.መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ፡-+251904033637/Office tel- +251112625267
የቡራዩ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት
ድርጅት / ቡራዩ/
___________________________________________________________________________________
Category : Energy, Generators, Pump Related, Purchase., Water and Water Works, Water Engineering Machinery/ Equipment and Tools
Posted Date : አዲስ ዘመን አርብ መጋቢት 11 ቀን 2012
Deadline : 2020-04-02