electronics gunchire

የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ መንግስት በጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በከተማው ከሚገኙት ሴ/መ/ቤቶች በ2012 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስና የውሃ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፡
በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር በመክፈል ፍቃድ ያሳደሳችሁ
የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ
በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 5,000/ አምስት ሺህ / እና በውሃ እቃዎች ብር 10,000/ አስር ሺ / ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው የጨረታ ማስከበርያው በጉ/ከ/አስ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም መሰራት አለበት፡፡
ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸው እቃዎች ጉ/ከ/ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃለው በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከመጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ከጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ::
ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን mቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው ::
ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸውን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስሪያ ቤቱ የጨረታው ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው::
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ ስከ 15 ኛው ቀን 8 ፡ 00 ሰዓት ድረስ ከጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8 ፡ 10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታው ከመክፈት አያስተጓጉለውም::
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የተጫረቱባቸው እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው::
ማሳሰቢያ፡
1 ኛ / ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሆነ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡ :
2ኛ/ በጨረታው ሂደት ውስጥ ተሻሽሎ የወጣው የክልሉ የግዥ መመሪያ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስ. ቁ. 0113320591 ይደውሉ
በደ/ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መ/ በጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት
ጉንችሬ
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 30 ቀን 2012
Deadline: May 22, 2020
© walia tender